ኤርምያስ 16:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በክፉ ሞት ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩምም፤ ነገር ግን በመሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍም ይወድቃሉ፤ በራብም ይጠፋሉ፤ ሬሳዎቻቸውም ለሰማይ ወፎችና ለዱር አራዊት መብል ይሆናሉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአደገኛ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይቀበሩም፤ በምድርም ላይ እንደ ጕድፍ ይጣላሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉ በሽታ ይሞታሉ፤ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉም በአሠቃቂ በሽታ ያልቃሉ፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ የሚቀብራቸው እንኳ አያገኙም፤ ሬሳቸው እንደ ጒድፍ በሜዳ ላይ ይከመራል፤ በጦርነትና በራብ ያልቃሉ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ምግብ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በክፉ ሞት ይሞታሉ፥ አይለቀስላቸውም አይቀበሩምም፥ በመሬትም ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ፥ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፥ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ። |
ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፤ በኃጥኣን ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት እጣል ዘንድ መረጥሁ።
ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት ይቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አውሬዎችም ሁሉ ይሰበሰቡባቸዋል።
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፤ ሬሳቸውም በመንገድ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
በዚህም ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምክር አፈርሳለሁ፤ በጠላቶቻቸው ፊት በጦርና ነፍሳቸውን በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ፤ ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።
በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም፤ አይቀበሩምም።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ሁሉ ለወንድሙና ለባልንጀራው ዓመተ ኅድገትን ለማድረግ እኔን አልሰማችሁም፤ እነሆ እኔ ለሰይፍና ለቸነፈር፥ ለራብም ዓመተ ኅድገትን አውጅባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል እበትናችኋለሁ።
ለጠላቶቻቸው እጅ፥ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
ስለዚህም ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ልጅ አይኖርለትም፥ ሬሳውም በቀን ለትኩሳት፥ በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።
ወደ ግብፅም ይገቡ ዘንድ፥ በዚያም ይቀመጡ ዘንድ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁ፤ ሁሉም ይጠፋሉ፤ በግብፅም ምድር ይወድቃሉ፤ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፤ ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለጥፋት፥ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
እነሆ ለመልካም ሳይሆን ለክፋት እተጋባቸዋለሁ፤ በግብፅም ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።
የሰዎቻችሁም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ፥ ማንም እንደማይሰበስበው ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል።
ለእስራኤል ቤት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኀይላችሁን ትምክሕት፥ የዐይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁንም ምኞት፥ መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።
ከአንቺም ሢሶው በቸነፈር ይሞታል፤ በመካከልሽም በራብ ያልቃል፤ ሢሶውም በዙሪያሽ በሰይፍ ይወድቃል፤ ሢሶውንም ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናለሁ፤ በኋላቸውም ሰይፍን እመዝዛለሁ።
በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት ሠርተዋልና እንደ ዕውር እስኪሄዱ ድረስ ሰዎችን አስጨንቃለሁ፣ ደማቸውም እንደ ትቢያ፥ ሥጋቸውም እንደ ጕድፍ ይፈስሳል።
እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኵሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።