Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 18:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አው​ሬ​ዎ​ችም በአ​ን​ድ​ነት ይቀ​ራሉ፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችና የም​ድር አው​ሬ​ዎ​ችም ሁሉ ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሁሉም በተራራ ላይ ለሚኖሩ ነጣቂ አሞሮች፣ ለዱርም አራዊት ይተዋሉ፤ አሞሮች በጋውን ሁሉ ሲበሉት ይባጃሉ፤ የዱር አራዊትም ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በተራራ ላይ ላሉ ነጣቂ ወፎች፥ ለምድርም አውሬዎች ይተዋሉ። ነጣቂ ወፎችም በጋውን ሁሉ ይበጁባቸዋል፤ የምድርም አውሬዎች ክረምቱን ሁሉ ሲበሉት ይከርማሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የወታደሮቻቸው ሬሳ ለወፎችና ለምድረ በዳ አራዊት ምግብ ይሆናል፤ በበጋ ወፎች፥ በክረምትም አራዊት ይቀራመቱታል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በተራራ ላይ ላሉ ነጣቂዎች ወፎች፥ ለምድርም አውሬዎች በአንድነት ይቀራሉ፥ ነጣቂዎችም ወፎች ይበጁባቸዋል፥ የምድርም አውሬዎች ሁሉ ይከርሙባቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 18:6
12 Referencias Cruzadas  

አንተ ግን በጦር ተወ​ግ​ተው ወደ መቃ​ብር ከሚ​ወ​ርዱ ብዙ ሙታን ጋር እንደ ረከሰ ሬሳ በተ​ራ​ሮች ላይ ትጣ​ላ​ለህ።


እነሆ፥ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ሀገር አሦ​ራ​ው​ያን አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ታ​ልና፤ ግን​ብ​ዋም ወድ​ቆ​አል፤


ከም​ሥ​ራ​ቅና ከሩቅ ሀገር ስለ መከ​ር​ሁት ምክር ዎፍን እጠ​ራ​ለሁ፤ ተና​ገ​ርሁ፤ አመ​ጣ​ሁም፤ ፈጠ​ርሁ፤ አደ​ረ​ግ​ሁም፤ አመ​ጣ​ሁት፤ መን​ገ​ዱ​ንም አቀ​ና​ሁ​ለት።


እና​ንተ የም​ድረ በዳ አራ​ዊት ሁሉ ኑ፤ እና​ንተ የዱር አራ​ዊት ሁሉ ብሉ።


ሰይ​ፍን ለመ​ግ​ደል፥ ውሾ​ች​ንም ለመ​ጐ​ተት፥ የሰ​ማ​ያ​ት​ንም ወፎች፥ የም​ድ​ር​ንም አራ​ዊት ለመ​ብ​ላ​ትና ለማ​ጥ​ፋት፥ አራ​ቱን ዓይ​ነት ጥፋት አዝ​ዝ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በክፉ ሞት ይሞ​ታሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም፤ ነገር ግን በመ​ሬት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ በራ​ብም ይጠ​ፋሉ፤ ሬሳ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለዱር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናሉ።”


የዚህ ሕዝብ ሬሳ ለሰ​ማይ ወፎ​ችና ለም​ድር አራ​ዊት መብል ይሆ​ናል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ቸው የለ​ምና።


በወ​ደ​ቀው ግንድ ላይ የሰ​ማይ ወፎች ሁሉ ይቀ​መ​ጣሉ፤ የም​ድ​ርም አራ​ዊት ሁሉ በቅ​ር​ን​ጫ​ፎቹ ላይ ይሆ​ናሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos