እግዚአብሔርም አለ፥ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት ራቁቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እንዲሁ በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምልክትና ተአምራት ይደረጋል።
ኤርምያስ 13:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅባት፤ በውኃውም ውስጥ አትንከራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ “ሄደህ ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅበት፤ ነገር ግን ውሃ አታስነካው” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይለኛል፦ “ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራን መታጠቂያ ለእራስህ ግዛ፥ ወገብህንም ታጠቀው፤ በውኃም ውስጥ አትንከረው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ከበፍታ የተሠራ መታጠቂያ ገዝተህ ታጠቀው፤ ውሃ ግን አታስነካው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ ሂድ፥ ከተልባ እግር የተሠራችን መታጠቂያ ለአንተ ግዛ፥ ወገብህንም ታጠቅባት፥ በውኃውም ውስጥ አትንከራት። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “ባሪያዬ ኢሳይያስ ሦስት ዓመት ራቁቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እንዲሁ በግብፅና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምልክትና ተአምራት ይደረጋል።
መታጠቂያ በሰው ወገብ ላይ እንደምትጣበቅ፥ እንዲሁ ለስም፥ ለመመኪያና ለክብር ሕዝብ ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ፥ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን አልሰሙም።”
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ሂድ፤ የሸክላ ሠሪ የሠራውን ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ አንሥቶ እጁንና እግሩን በገዛ እጁ አስሮ እንዲህ አለ፥ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ የዚህን መታጠቂያ ጌታ አይሁድ በኢየሩሳሌም እንዲህ ያስሩታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል።”