በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
ኢሳይያስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ በላያቸው የነበረው ቀንበር ተነሥቶአልና፥ በጫንቃቸው የነበረውንም፥ የአስጨናቂዎችንም በትር መልሶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፣ የከበዳቸውን ቀንበር፣ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፣ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጦረኞች ጫማ ሁሉ፤ በደም የተለወሰ ልብስም ሁሉ፤ ለእሳት ይዳረጋል፤ ይማገዳልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቀድሞ ዘመን ምድያማውያንን ድል እንዳደረግህ ሁሉ፥ አሁንም በሕዝብህ ላይ የተጫነውን የአገዛዝ ቀንበርና በትከሻቸው ላይ የተቃጣውን በትር ሰባበርክ፤ ሕዝብህን በማስጨነቅ ይገዛ የነበረውን ድል አደረግህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድያም ጊዜ እንደሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር ያስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል። |
በሰይፍህም ትኖራለህ፤ ለወንድምህም ትገዛለህ፤ ነገር ግን ቀንበሩን ከአንገትህ ልትጥል ብትወድድ ከእርሱ ጋር ተስማማ።”
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፤ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ፤ ቀንበሩም ከእነርሱ ላይ ይነሣል፤ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።”
ከሚከቧችሁ ጋር ጠላቶች እንዳይሆኗችሁ ከሞዓብ የተሰደዱትን ከእናንተ ጋር አታስቀምጡ፤ ሰልፈኞች አልቀዋልና፤ በሀገሪቱ ሁሉ የነበረውም አለቃ ጠፍቶአልና።
በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሽ፤ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለሽማግሌዎቻቸው አልራራሽም፤ ቀንበራቸውንም እጅግ አክብደሻል።
የአስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን ይበላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኀኒትሽና ታዳጊሽ፥ የያዕቆብን ኀይል የምደግፍ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
አንቺ ግን ሰማያትን የፈጠረውን፥ ምድርንም የመሠረታትን ፈጣሪሽን እግዚአብሔርን ረስተሻል፤ ያጠፋሽ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሻል፤ ይቈጣሽ ዘንድ መክሮአልና፤ አሁን የሚያስጨንቅሽ ቍጣው የት አለ?
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፤ እስራትህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለሌላ አትገዛም።
በዙሪያው ያላችሁ ሁሉ ስሙንም የምታውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠንካራውም ሽመል፥ እንዴት ተሰበረ! ብላችሁ አልቅሱለት።
ባሪያዎች ከነበራችሁበት ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ በግልጽም አወጣኋችሁ።