የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
ኢሳይያስ 47:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፥ “የመንግሥታት እመቤት” አትባዪምና በድንጋጤ ዝም ብለሽ ተቀመጪ፤ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት ተብለሽ አትጠሪም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፦ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎን ሆይ! በጨለማ ውስጥ ጸጥ ብለሽ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ‘የመንግሥታት ንግሥት’ ብለው አይጠሩሽም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፦ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ። |
የሰማይም ከዋክብትና ኦሪዎን፥ የሰማይ ሠራዊትም ሁሉ ብርሃናቸውን አይሰጡም፤ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፤ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
“ባቢሎንን የወፎች መኖሪያ አደርጋታለሁ፤ እንደ ኢምንትም ትሆናለች፤ በጥፋትም እንደ ረግረግ ጭቃ አደርጋታለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ይህንም ሙሾ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፤ እንዲህም ትላለህ፥ “አስጨናቂ እንዴት ዐረፈ! አስገባሪም እንዴት ጸጥ አለ!
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስላሳና ቅምጥል አትባዪምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
አንቺም፥ “እኔ ለዘለዓለም እመቤት እሆናለሁ” ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላሰብሽም፤ ፍጻሜውንም አላስታወስሽም።
ከእነርሱም የሐሤትን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምጽና የሴት ሙሽራን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ።
“ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ ተመልታ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፤ አሕዛብን ትገዛ የነበረች፥ አውራጃዎችንም ትገዛ የነበረች ገባር ሆናለች።
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢየሩሳሌም መሳፍንቱንና ደናግሉን ወደ ምድር አወረዷቸው።
ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ሐዘን ስጡአት። በልብዋ ‘ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ባልቴትም አልሆንም፤ ሐዘንም ከቶ አላይም፤’ ስላለች፥