Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 47:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባቢሎን ሆይ! በጨለማ ውስጥ ጸጥ ብለሽ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ‘የመንግሥታት ንግሥት’ ብለው አይጠሩሽም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት ተብለሽ አትጠሪም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፦ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፥ “የመ​ን​ግ​ሥ​ታት እመ​ቤት” አት​ባ​ዪ​ምና በድ​ን​ጋጤ ዝም ብለሽ ተቀ​መጪ፤ ወደ ጨለ​ማም ውስጥ ግቢ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ፦ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 47:5
25 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ በምጣራበት ጊዜ አታሳፍረኝ፤ ክፉዎች ግን ይፈሩ፤ ጸጥ ብለውም ወደ ሲኦል ይውረዱ።


ጸጥ ብላችሁ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ዕወቁ፤ በሕዝቦች መካከል ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


እያንዳንዱ ኮከብና የከዋክብት ክምችቱ ብርሃን መስጠቱን ያቆማል፤ የንጋት ፀሐይ ገና ከመውጣትዋ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም።


ባቢሎንን ረግረግ ስለማደርጋት የአልቅት መፈልፈያ ትሆናለች፤ ባቢሎንን ሁሉን ነገር ጠራርጎ በሚወስድ መጥረጊያ እጠርጋታለሁ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


በባቢሎን ንጉሥ ላይ እንዲህ እያላችሁ ታፌዙበታላችሁ፦ “እነሆ ጨቋኙ ንጉሥ ወደቀ! ከእንግዲህ ወዲህ ማንንም አይጨቊንም!


ጥንድ ጥንድ ሆነው በፈረስ የተቀመጡ ሰዎች እነሆ በድንገት ይመጣሉ፤ ዘብ ጠባቂውም “እነሆ ባቢሎን ወደቀች! የሚሰግዱላቸውም ጣዖቶች ሁሉ ተሰባብረው ወደቁ” የሚል ዜና ያስተላልፋል።


መርከበኞች ያበለጸጉአችሁ እናንተ የደሴቲቱ ሕዝብና የሲዶን ነጋዴዎች በሐዘን ጸጥ በሉ!


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “አንቺ በማንም ያልተደፈርሽ የባቢሎን ከተማ ሆይ! ወርደሽ በዐቧራ ላይ ተቀመጪ፤ ወርደሽ በዙፋን ላይ ሳይሆን፤ በመሬት ላይ ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅምጥልና ለስላሳ መባልሽ ይቀራል።


‘እኔ ለዘለዓለም ንግሥት ሆኜ እኖራለሁ’ አልሽ፤ ስላደረግሽው ድርጊት ምንም አላሰብሽም፤ የተግባርሽም ውጤት ምን እንደሚሆን አላስተዋልሽም።


የደስታና የሐሤት ድምፅ፥ የሠርግ ዘፈንም ድምፅ እንዳይኖር፥ ማንም ሰው እህል እንዳይፈጭ፥ ወይም በሌሊት መብራት እንዳያበራ አደርጋለሁ።


የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ዝም ብለን መቀመጣችን ለምንድን ነው? አምላካችን እግዚአብሔር ሞት ፈርዶብናል፤ እርሱን ስለ በደልን የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ አድርጎናል። ኑ! ወደተመሸጉ ከተሞች ሮጠን እዚያ እንሙት፤


በአንድ ወቅት በሕዝብ ተሞልታ የነበረችው ከተማ እንዴት ብቸኛ ሆነች! በሕዝቦች መካከል ታላቅ የነበረችው እንዴት ባል እንደ ሞተባት ሴት ሆነች! በአውራጃዎች መካከል ልዕልት የነበረችው፥ አሁን እርስዋ እንደ ባሪያ ሆነች።


የኢየሩሳሌም ከተማ ሽማግሌዎች ጸጥ ብለው በምድር ላይ ተቀመጡ፤ እነርሱ በራሳቸው ላይ ትቢያ ነስንሰው ማቅ ለበሱ፤ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች አንገታቸውን ደፉ።


እግዚአብሔር በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ስለዚህ የዓለም ሕዝብ ሁሉ በፊቱ ጸጥ ይበል።


እግዚአብሔር ከተቀደሰ መኖሪያው ለመምጣት ስለ ተነሣ ሁላችሁም በፊቱ ዝም በሉ።


የአሳፋሪ ድርጊታቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ፥ እንደ ተቈጣ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም እንደሚጠብቃቸውና፥ እንደሚንከራተቱ ኮከቦች ናቸው።


“ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”


እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።


“ሰው ድልን የሚያገኘው በኀይሉ ስላልሆነ እግዚአብሔር የታማኞቹን እርምጃዎች ይጠብቃል፤ ክፉዎች ግን ወደ ጨለማ ይጣላሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos