ኢሳይያስ 45:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድርጌ ሠራሁህ፤ ምድርን የሚያርስ ሁልጊዜ ያርሳልን? ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? እጅ የለህምና መሥራት አትችልም ይለዋልን? ጭቃ ሠሪውን ይከራከረዋልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዐፈር ሸክላዎች መካከል፣ ከሠሪው ጋራ ክርክር ለሚገጥም ወዮለት! ጭቃ፣ ሸክላ ሠሪውን፣ ‘ምን እየሠራህ ነው?’ ይለዋልን? የምትሠራውስ ሥራ፣ ‘እጅ የለህም’ ይልሃልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ እጅ የለውም ይላልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! እርሱ እኮ ከሸክላ ዕቃዎች እንደ አንዱ ነው፤ አንድ የሸክላ ሥራ ሸክላ ሠሪውን “ምንድን ነው የምታደርገው? እጀታውስ የት አለ?” ብሎ ሊጠይቅ ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሠሪው ጋር ለሚታገል ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው። ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? ወይስ ሥራህ፦ እጅ የለውም ይላልን? |
“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”
“በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይነሣልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህም ዘንግ በሚመቱበት ላይ እንደ መነሣት፥ በትርም ዕንጨት አይደለሁም እንደ ማለት ነው።”
ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፥ “አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ የተደረገ አድራጊውን፥ “በማስተዋል አላሳመርኸኝም” ይለዋልን?
ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ መልሰሃል፤ ለኀጢአታችንም አሳልፈህ ሰጥተኸናል።
“የእስራኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? እነሆ ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፥ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ አላችሁ።
የይሁዳንም ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይችንም ሀገር ያፈርሳታል፤ ሰውና እንስሳም ያልቃሉ ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።
ባቢሎን ሆይ! በመከራው ተይዘሽ ጠፋሽ፤ አንቺም ይህ እንደመጣብሽ አላወቅሽም፤ እግዚአብሔርን ተቃውመሽዋልና ተገኝተሻል፤ ተይዘሽማል።