Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እርሱ ቢያ​ርቅ የሚ​መ​ልስ ማን ነው? እር​ሱ​ንስ፦ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ቢነጥቅ፣ ማን ይከለክለዋል? ‘ምን መሥራትህ ነው?’ የሚለውስ፣ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የፈለገውን ቢወስድ ማንም አይከለክለውም፤ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚደፍርም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:12
18 Referencias Cruzadas  

“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን?


እርሱ ሁሉን ቢገ​ለ​ብጥ፥ ምን አደ​ረ​ግህ? የሚ​ለው ማን ነው?


“ስለ ፍርድ የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እርሱ የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ር​ጋ​ልና።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሳ​ቡን ማን ያው​ቃል? ወይስ ማን ተማ​ከ​ረው?


“እርሱ ዕረ​ፍ​ትን ይሰ​ጣል፤ የሚ​ፈ​ር​ድስ ማን ነው? በሕ​ዝብ ወይም በሰው ዘንድ ፊቱን ቢሰ​ውር የሚ​ያ​የው ማን ነው?


ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?


“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ይህ ሸክላ ሠሪ እን​ደ​ሚ​ሠራ በውኑ እኔ በእ​ና​ንተ ዘንድ መሥ​ራት አይ​ቻ​ለ​ኝ​ምን? እነሆ ጭቃው በሸ​ክላ ሠሪ እጅ እን​ዳለ፥ እን​ዲሁ እና​ንተ በእኔ እጅ አላ​ችሁ።


አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።


እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚ​ሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስ​ቀ​ድ​መን የተ​ወ​ሰን በእ​ርሱ ርስ​ትን ተቀ​በ​ልን።


አዎን አባት ሆይ! ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።


ከዚህ በላይ በደ​ለኛ እን​ዳ​ል​ሆ​ንሁ፥ አንተ ታው​ቃ​ለህ። ነግር ግን ከእ​ጅህ የሚ​ያ​መ​ልጥ ማን ነው?


ንጉሥ እንደ መሆኑ ኀይል አለ​ውና፤ ይህ​ንስ ለምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? ማን ይለ​ዋል?


ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?


ንጉ​ሡም፥ “እና​ንተ የሶ​ር​ህያ ልጆች! በእ​ኔና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምን አለኝ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዳዊ​ትን ርገ​መው ብሎ አዝ​ዞ​ታ​ልና ይር​ገ​መኝ፤ ለም​ንስ እን​ዲህ ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?” አለ።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ራቁ​ቴን ወጥ​ቻ​ለሁ፥ ራቁ​ቴ​ንም ወደ ምድር እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰጠ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነሣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ብ​ሔር ስም የተ​ባ​ረከ ይሁን።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios