Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 29:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይህ የእ​ና​ንተ ጠማ​ም​ነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የም​ት​ቈ​ጠሩ አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? በውኑ ሥራ ሠሪ​ውን፥ “አል​ሠ​ራ​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን? ወይስ የተ​ደ​ረገ አድ​ራ​ጊ​ውን፥ “በማ​ስ​ተ​ዋል አላ​ሳ​መ​ር​ኸ​ኝም” ይለ​ዋ​ልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እናንተ ነገሮችን ትገለብጣላችሁ ሸክላ ሠሪውን እንደ ሸክላ ትመለከታላችሁ! ለመሆኑ፣ ተሠሪ ሠሪውን፣ “እርሱ አልሠራኝም” ይለዋልን? ሸክላ የሠራውን፣ “እርሱ ምንም አያውቅም” ይለዋልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ “አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ “አታስተውልም” ይለዋልን?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እናንተ ሁሉን ነገር ትገለባብጣላችሁ። ሸክላ ሠሪው ከሸክላው አይበልጥምን? አንድ የተሠራ ሥራ ሠሪውን “አንተ አልሠራኸኝም” ይለዋልን? ወይስ ደግሞ የሸክላ ዕቃ ሸክላ ሠሪውን “ሥራህን አታውቅም” ይለዋልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ይህ የእናንተ ጠማምነት ነው፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃ የምትቈጠሩ አይደላችሁምን? በውኑ ሥራ ሠሪውን፦ አልሠራኸኝም ይለዋልን? ወይስ የተደረገው አድራጊውን፦ አታስተውልም ይለዋልን?

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 29:16
9 Referencias Cruzadas  

እህ​ልን ከም​ድር ያወጣ ዘንድ፥ ለም​ለ​ሙን ለሰው ልጆች አገ​ል​ግ​ሎት፥ ሣር​ንም ለእ​ን​ስሳ ያበ​ቅ​ላል።


“በውኑ መጥ​ረ​ቢያ በሚ​ቈ​ር​ጥ​በት ሰው ላይ ይነ​ሣ​ልን? ወይስ መጋዝ በሚ​ስ​በው ሰው ላይ ይጓ​ደ​ዳ​ልን? ይህም ዘንግ በሚ​መ​ቱ​በት ላይ እንደ መነ​ሣት፥ በት​ርም ዕን​ጨት አይ​ደ​ለ​ሁም እንደ ማለት ነው።”


እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለ​ምን ያጠ​ፋ​ታል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ጋ​ታል፤ ይገ​ለ​ብ​ጣ​ት​ማል፤ በእ​ር​ስ​ዋም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ይበ​ት​ናል።


አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፥ አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን፤ አን​ተም ሠሪ​ያ​ችን ነህ፤ እኛም ሁላ​ችን የእ​ጅህ ሥራ ነን።


በአ​ጧ​ቸ​ውም ጊዜ ኢያ​ሶ​ንን ጐተ​ቱት፤ በዚ​ያም የነ​በ​ሩ​ትን ጓደ​ኞች ጭምር ወደ ሹሞቹ ወሰ​ዱ​አ​ቸው፤ እየ​ጮ​ኹም እን​ዲህ ይሉ ነበር፥ “ዓለ​ምን የሚ​ያ​ው​ኳት እነ​ዚህ ናቸው፤ ወደ​ዚ​ህም መጥ​ተ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos