Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 33:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አንተ፦ ‘ቃሌን ሁሉ ለምን አይ​ሰ​ማ​ኝም?’ ትላ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የሰውን አቤቱታ እንደማይሰማ፣ ለምን ታማርርበታለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 አንተ፦ ‘በፍጹም ለቃሌ መልስ አይሰጥም’ ብለህ፥ ስለምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ታዲያ፥ ‘እግዚአብሔር የሰውን አቤቱታ አይሰማም’ በማለት ለምን በእግዚአብሔር ላይ ታማርራለህ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አንተ፦ ለቃሌ ሁሉ አይመልስልኝም ብለህ፥ ስለ ምን ከእርሱ ጋር ትከራከራለህ?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 33:13
21 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲህ እለ​ዋ​ለሁ፦ ኀጢ​ኣ​ተኛ እን​ድ​ሆን አታ​ስ​ተ​ም​ረኝ፤ ለም​ንስ እን​ደ​ዚህ ፈረ​ድ​ህ​ብኝ?


ክፋ​ቴን ትፈ​ላ​ለግ ዘንድ፥ ኀጢ​ኣ​ቴ​ንም ትመ​ረ​ምር ዘንድ፥


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍለጋ ልት​መ​ረ​ምር ትች​ላ​ለ​ህን? ወይስ ሁሉን የሚ​ችል አም​ላክ ወደ ፈጠ​ረው ፍጥ​ረት ፍጻሜ ትደ​ር​ሳ​ለ​ህን?


“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”


እርሱ ቢያ​ርቅ የሚ​መ​ልስ ማን ነው? እር​ሱ​ንስ፦ ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ? የሚ​ለው ማን ነው?


ቃሌን እን​ዴት ይሰ​ማ​ኛል? እን​ዴ​ትስ ይተ​ረ​ጕ​መ​ዋል?


ንጉሥ ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይለ​ዋል፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ምል ሁሉ ይከ​ብ​ራል፥ ዐመ​ፅን የሚ​ና​ገር አፍ ይዘ​ጋ​ልና።


“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድ​ርጌ ሠራ​ሁህ፤ ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሁል​ጊዜ ያር​ሳ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን፦ ምን ትሠ​ራ​ለህ? እጅ የለ​ህ​ምና መሥ​ራት አት​ች​ልም ይለ​ዋ​ልን? ጭቃ ሠሪ​ውን ይከ​ራ​ከ​ረ​ዋ​ልን?


በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ።


ባቢ​ሎን ሆይ! በመ​ከ​ራው ተይ​ዘሽ ጠፋሽ፤ አን​ቺም ይህ እን​ደ​መ​ጣ​ብሽ አላ​ወ​ቅ​ሽም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ተቃ​ው​መ​ሽ​ዋ​ልና ተገ​ኝ​ተ​ሻል፤ ተይ​ዘ​ሽ​ማል።


እኔ በማ​ደ​ር​ግ​ብሽ ወራት ልብሽ ይታ​ገ​ሣ​ልን? ወይስ እጆ​ችሽ ይጸ​ና​ሉን? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ አደ​ር​ገ​ው​ማ​ለሁ።


ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመጣ ከሆነ ግን ልታ​ፈ​ር​ሱት አት​ች​ሉም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጋር እን​ደ​ሚ​ጣላ አት​ሁኑ።”


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዐሳ​ቡን ማን ያው​ቃል? ወይስ ማን ተማ​ከ​ረው?


ሰው ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ት​ከ​ራ​ከ​ረው አንተ ምን​ድን ነህ? ሥራ ሠሪ​ውን እን​ዲህ አታ​ድ​ር​ገኝ ሊለው ይች​ላ​ልን?


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​ስ​ቀ​ና​ውን? በውኑ እኛ ከእ​ርሱ እን​በ​ረ​ታ​ለን?


“ምስ​ጢሩ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የተ​ገ​ለ​ጠው ግን የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios