አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና፤ ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
ኢሳይያስ 44:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጣዖታትን የሚቀርጹ ያንጊዜ አይኖሩም፤ የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩም ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ የማይረባቸውን የራሳቸውን ፍላጎት የሚያደርጉ ሁሉ ያፍራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጣዖት የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች፣ የሚሠሩባቸውም ነገሮች ዋጋ ቢስ ናቸው፤ የሚናገሩላቸው ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም ያፍራሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይጠቅማቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያስተውሉም ደግሞ አያውቁም፥ ስለዚህ ያፍራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጣዖቶችን የሚሠሩ ሁሉ ከንቱ ናቸው፤ ከፍተኛ ግምት የሚሰጡአቸው ጣዖቶቻቸውም ዋጋቢሶች ናቸው፤ በዚህም ኀፍረት ይደርስባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ከንቱዎች ናቸው፥ የወደዱትም ነገር አይረባቸውም፥ ምስክሮቻቸውም አያዩምና አያውቁም፥ ስለዚህ ያፍራሉ። |
አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና፤ ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፥ “አምላኮቻችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ፤ ፈጽመውም ያፍራሉ።
አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አለቆችም ተከማቹ፤ ይህን ማን ይናገራል? የቀድሞውንስ ማን ይነግራችኋል? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፤ ሰምተውም፦ እውነትን ይናገሩ።
እንግዲህ ልባቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእነርሱም ነፍሱን ለማዳን የሚችል ማንም እንደሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚልም እንደሌለ ተመልከቱ።
እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ፥ ተሰብስባችሁ ኑ፤ በአንድነትም ተማከሩ፤ የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ ዕውቀት የላቸውም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪያዎች ይበላሉ፤ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ ባሪያዎች ይጠጣሉ፤ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ ባሪያዎች ደስ ይላቸዋል፤ እናንተ ግን ትጐሰቍላላችሁ፤
በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰጥና ሊያጠግብ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
አሕዛብ አማልክት ያልሆኑ አማልክቶቻቸውን ይለውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብራቸውን ለማይረባ ነገር ለወጡ።
ሌባ በተያዘ ጊዜ እንደሚያፍር፤ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች፥ እነርሱና ንጉሦቻቸውም፥ አለቆቻቸውም፥ ካህናቶቻቸውም፥ ነቢያቶቻቸውም ያፍራሉ።
ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
እግዚአብሔርን የሚመስለው የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው የዚህ ዓለም አምላክ ልባቸውን አሳውሮአልና።
“በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ የሠራተኛ እጅ ሥራን፥ የተቀረፀ ወይም ቀልጦ የተሠራ ምስልን የሚያደርግ፥ በስውርም የሚያቆመው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝቡም ሁሉ መልሰው አሜን ይላሉ።
በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትንም፥ የማይበሉትንም፥ የማያሸቱትንም፥ በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ሌሎች አማልክት ታመልካላችሁ።