Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 43:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አሕ​ዛብ ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​በ​ሰቡ፤ አለ​ቆ​ችም ተከ​ማቹ፤ ይህን ማን ይና​ገ​ራል? የቀ​ድ​ሞ​ው​ንስ ማን ይነ​ግ​ራ​ች​ኋል? ይጸ​ድቁ ዘንድ ምስ​ክ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ያምጡ፤ ሰም​ተ​ውም፦ እው​ነ​ትን ይና​ገሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሕዝብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰብ፤ ሰውም ይከማች፤ ከእነርሱ አስቀድሞ ይህን የነገረን፣ የቀድሞውን ነገር ያወጀልን ማን ነው? ሌሎችን ሰምተው፣ “እውነት ነው” እንዲሉ፣ ትክክለኝነታቸውም እንዲረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፥ ወገኖችም ይከማቹ፤ ከመካከላቸው ይህን የሚናገር፥ የቀድሞውንስ ነገር የሚያሳየን ማን ነው? እንዲጸድቁ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፥ ሰምተውም፦ “እውነት ነው” ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሕዝቦች ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፤ ከእነርሱ መካከል የአሁንና የቀድሞዎቹን ነገሮች አስቀድሞ የተናገረና የገለጠ ማነው? እውነተኛነታቸውን ለማረጋገጥ ምስክሮቻቸውን ያምጡ። እነርሱም ሰምተው እውነት ነው ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ ወገኖችም ይከማቹ፥ ከመካከላቸው ይህን የሚናገር፥ የቀድሞውንስ ነገር የሚያሳየን ማን ነው? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፥ ሰምተውም፦ እውነት ነው ይበሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 43:9
17 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ እንደ ቸር​ነ​ትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕ​ረ​ት​ህም ብዛት ኀጢ​አ​ቴን ደም​ስስ።


እና​ንተ አሕ​ዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እና​ን​ተም አለ​ቆች ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ ምድ​ርና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ፥ ዓለ​ምና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ አለ​ቆች ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት ቀር​በው ፍር​ድን ይና​ገሩ።


አሳ​ስ​በኝ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሆነን እን​ፋ​ረድ፤ እን​ድ​ት​ጸ​ድቅ አስ​ቀ​ድ​መህ በደ​ል​ህን ተና​ገር።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


በመ​ጀ​መ​ሪያ መጨ​ረ​ሻ​ውን፥ ከጥ​ን​ትም ያል​ተ​ደ​ረ​ገ​ውን እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ምክሬ ትጸ​ና​ለች፤ የመ​ከ​ር​ሁ​ት​ንም ሁሉ አደ​ር​ጋ​ለሁ እላ​ለሁ።


ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ይሰ​ማሉ፤ ይህን ማን ነገ​ራ​ቸው? አን​ተን በመ​ው​ደድ የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን ዘር አስ​ወ​ግድ ዘንድ ፈቃ​ድ​ህን በባ​ቢ​ሎን ላይ አደ​ረ​ግሁ።


የቀ​ድ​ሞ​ውን ነገር ከጥ​ንት ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ከአ​ፌም ወጥ​ቶ​አል፤ ድን​ገ​ትም ያደ​ረ​ግ​ሁት ምስ​ክር ሆኖ​አል፤ እር​ሱም ተፈ​ጽ​ሞ​አል።


እና​ንተ በዙ​ሪያ ያላ​ችሁ አሕ​ዛብ ሁሉ፥ ፈጥ​ና​ችሁ ኑ፥ ተሰ​ብ​ሰቡ፤ የዋ​ሃ​ንም ሰል​ፈ​ኞች ይሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos