Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 41:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እና​ንተ ከየት ናችሁ? ከየ​ትስ ሠሯ​ችሁ? ከም​ድር የሚ​መ​ር​ጧ​ች​ሁም የረ​ከሱ አይ​ደ​ሉ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እነሆ፤ እናንተ ከምንም የማትቈጠሩ ናችሁ፤ ሥራችሁ ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ነው፤ የመረጣችሁም አስጸያፊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እናንተም ሆናችሁ ድርጊታችሁ በእርግጥ ከንቱ ነው፤ እናንተን ማምለክ የሚሹም አጸያፊዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 እነሆ፥ እንዳልነበረ ናችሁ፥ ሥራችሁም ከንቱ ነው፥ የሚመርጣችሁም አስጸያፊ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 41:24
17 Referencias Cruzadas  

ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።


ለአ​ንተ የም​ስ​ጋና መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም በከ​ንቱ ይሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


በአ​ንድ ጊዜ ሰን​ፈ​ዋል፥ ደን​ቍ​ረ​ው​ማል፤ ጣዖ​ታት የሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ሩት የእ​ን​ጨት ነገር ብቻ ነው።


በግምባርዋም ምስጢር የሆነ ስም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የጋለሞታዎችና የምድር ርኵሰት እናት” ተብሎ ተጻፈ።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


ወጥ​ተ​ውም በእኔ ያመ​ፁ​ብ​ኝን ሰዎች ሬሳ​ቸ​ውን ያያሉ፤ ትላ​ቸው አይ​ሞ​ትም፤ እሳ​ታ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ፋም፤ ለሥጋ ለባ​ሽም ሁሉ ምሳሌ ይሆ​ናሉ።”


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ የሠ​ራ​ተኛ እጅ ሥራን፥ የተ​ቀ​ረፀ ወይም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በስ​ው​ርም የሚ​ያ​ቆ​መው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መል​ሰው አሜን ይላሉ።


ርኩ​ስን ነገር ወደ ቤትህ አታ​ግባ፤ እንደ እር​ሱም ርጉም ትሆ​ና​ለህ፤ ርጉም ነውና መጸ​የ​ፍን ተጸ​የ​ፈው፤ መጥ​ላ​ት​ንም ጥላው።


ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤ ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


አገ​ጣ​ጥ​መው የሚ​ሠ​ሩት ሥራ ከንቱ ነው፤ በተ​ጐ​በኙ ጊዜም ይጠ​ፋሉ።


የአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ምስል በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠ​ራ​ባ​ቸ​ውን ብር​ንና ወር​ቅን፥ አት​መኝ፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ርኩስ ነውና እን​ዳ​ት​በ​ድ​ል​በት ከእ​ርሱ ምንም አት​ው​ሰድ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios