Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 44:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከሰ​ዎች መካ​ከል ደን​ቆ​ሮ​ዎች ሁሉ ይሰ​ብ​ሰቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ይቁሙ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የእጅ ጥበብ ባለሙያው ሰው እንጂ ሌላ አይደለም፤ እርሱና መሰሎቹም ያፍራሉ፤ ሁሉም ተሰብስበው በአንድ ላይ ይቁሙ፤ ይደነግጣሉ፤ ይዋረዳሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነሆ፥ ባልንጀሮቹ ሁሉ ያፍራሉ፥ ባለሙያዎቹም ከሰው ወገን ናቸው፤ ሁሉም ተሰብስበው ይቁሙ፤ ይፈራሉ በአንድነትም ያፍራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እነርሱንም የሚያመልኩ ሁሉ ያፍራሉ፤ ጣዖትን የሚሠሩ ሰዎች እንጂ ሌላ አይደለም፤ ሁሉም ይሰብሰቡና በፊቴ ይቁሙ፤ ሁሉም በፍርሃት ይዋጣሉ፤ ያፍራሉም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነሆ፥ ባልንጀሮቹ ሁሉ ያፍራሉ፥ ሠራተኞቹም ከሰዎች ወገን ናቸው፥ ሁላቸው ተሰብስበው ይቁሙ፥ ይፈራሉ በአንድነትም ያፍራሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 44:11
22 Referencias Cruzadas  

ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


ባሕር በሞ​ላዋ፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይና​ወጡ።


በወ​ደ​ዱ​አ​ቸው ጣዖ​ታት ያፍ​ራ​ሉና፥ በፈ​ለ​ጉ​አ​ቸ​ውም የአ​ድ​ባር ዛፎች ዕፍ​ረት ይይ​ዛ​ቸ​ዋ​ልና፤


በተ​ቀ​ረ​ጹ​ትም ምስ​ሎች የሚ​ታ​መኑ፥ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ያፍ​ራሉ።


ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ቀ​ርጹ ያን​ጊዜ አይ​ኖ​ሩም፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል የሚ​ሠ​ሩም ሁሉ ከን​ቱ​ዎች ናቸው፤ የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን የራ​ሳ​ቸ​ውን ፍላ​ጎት የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


የሚ​ቃ​ወ​ሙት ሁሉም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ አፍ​ረ​ውም ይሄ​ዳሉ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይበ​ላሉ፤ እና​ንተ ግን ትራ​ባ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይጠ​ጣሉ፤ እና​ንተ ግን ትጠ​ማ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ላ​ችሁ፤


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀ​ትን አጥ​ቶ​አል፥ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ሐሰ​ተ​ኞች ጣዖ​ታ​ትን ሠር​ተ​ዋ​ልና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የላ​ቸ​ው​ምና።


ዳግ​መ​ኛም በደሉ፤ ጠራቢ በሚ​ሠ​ራው አም​ሳል ከወ​ር​ቃ​ቸ​ውና ከብ​ራ​ቸው ጣዖ​ትን ሠሩ፤ እን​ዲ​ህም አሉ “ሰውን ሠዉ፤ ላሙ ግን አል​ቋል።”


በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos