Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 115:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የሕ​ይ​ወ​ትን ጽዋ እቀ​በ​ላ​ለሁ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እጠ​ራ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የእነርሱ ጣዖታት ግን የሰው እጅ ያበጃቸው፣ ብርና ወርቅ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የአሕዛብ ጣዖታቶች የወርቅና የብር፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እነርሱ የሚያመልኩአቸው ጣዖቶች ግን በሰው እጅ ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 115:4
23 Referencias Cruzadas  

የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር።


እስከ ሠር​ክም ድረስ ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር፤ ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስና የሚ​ያ​ደ​ም​ጥም አል​ነ​በ​ረም። ከዚ​ህም በኋላ መሥ​ዋ​ዕት በሚ​ያ​ር​ግ​በት ጊዜ ኤል​ያስ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ በቃ​ችሁ፤ ወግዱ፤ ሂዱም፥ እኔም መሥ​ዋ​ዕ​ቴን እሠ​ዋ​ለሁ” አላ​ቸው።


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ላይ ጥለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና፤ ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


በሰ​ውም እጅ በተ​ሠሩ በም​ድር አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ላይ እን​ደ​ሚ​ና​ገር መጠን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አም​ላክ ላይ ተና​ገረ።


ባሕር በሞ​ላዋ፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይና​ወጡ።


አማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለ​ዋል፤ የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማ​ል​ክት አል​ነ​በ​ሩ​ምና ስለ​ዚህ አጥ​ፍ​ተ​ዋ​ቸ​ዋል።


በተ​ቀ​ረ​ጹ​ትም ምስ​ሎች የሚ​ታ​መኑ፥ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ያፍ​ራሉ።


ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ሠሩ፥ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ውን ምስል የሚ​ቀ​ር​ጹና በእ​ነ​ር​ሱም የተ​ሠሩ ሁሉ ይደ​ር​ቃሉ።


እን​ግ​ዲህ ልባ​ቸው አመድ እንደ ሆነና እንደ በደሉ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ነፍ​ሱን ለማ​ዳን የሚ​ችል ማንም እን​ደ​ሌለ ዕወቁ፤ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ” የሚ​ልም እን​ደ​ሌለ ተመ​ል​ከቱ።


ጣዖ​ታ​ትን የሚ​ቀ​ርጹ ያን​ጊዜ አይ​ኖ​ሩም፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን ምስል የሚ​ሠ​ሩም ሁሉ ከን​ቱ​ዎች ናቸው፤ የማ​ይ​ረ​ባ​ቸ​ውን የራ​ሳ​ቸ​ውን ፍላ​ጎት የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


ይህ ደግሞ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ነው፤ ሠራ​ተኛ ሠራው፤ እር​ሱም አም​ላክ አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ርያ ሆይ! እን​ቦ​ሳሽ ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዞ​አ​ልና።


አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።


ከዚ​ህም በኋላ የከ​ተ​ማው ጸሓፊ ተነ​ሥቶ ሕዝ​ቡን ጸጥ አሰ​ኝቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የኤ​ፌ​ሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤ​ፌ​ሶን ከተማ ታላ​ቂ​ቱን አር​ጤ​ም​ስ​ንና ከሰ​ማይ የወ​ረ​ደ​ውን ጣዖ​ት​ዋን እን​ደ​ም​ት​ጠ​ብቅ የማ​ያ​ውቅ ማነው?


በዚ​ያም የማ​ያ​ዩ​ትን፥ የማ​ይ​ሰ​ሙ​ት​ንም፥ የማ​ይ​በ​ሉ​ት​ንም፥ የማ​ያ​ሸ​ቱ​ት​ንም፥ በሰው እጅ ከእ​ን​ጨ​ትና ከድ​ን​ጋይ የተ​ሠ​ሩ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos