ኢሳይያስ 3:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ይሆናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁንብሽ፤ በወርቅ መታጠቂያሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸላሽም ፋንታ ቡሃነት ይውጣብሽ፤ በሐር መጐናጸፊያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሽቱ ፈንታ ግማት፣ በሻሽ ፈንታ ገመድ፣ አምሮ በተሠራ ጠጕር ፈንታ ቡሓነት፣ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሽቶ ፈንታ ግማት፤ በሻሽ ፈንታ ገመድ፤ አምሮ በተሠራ ጠጉር ፈንታ ቡሀነት፤ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፤ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሽቶ ፈንታ ግማት፥ በጥሩ መታጠቂያ ፈንታ ገመድ፥ በጐፈሬ ፈንታ ቡሃነት፥ በመጐናጸፊያ ፈንታ ማቅ፥ በውበትም ፈንታ ጠባሳ መሆን ይመጣባቸዋል! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ይሆናል፥ በሽቱ ፋንታ ግማት፥ በመታጠቂያውም ፋንታ ገመድ፥ ጠጕርንም በመንቀስ ፋንታ ቡሀነት፥ በመጎናጸፊያ ፋንታ ማቅ፥ በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል። |
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
በየመንገድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየሰገነቶችዋም አልቅሱ፤ በየአደባባዮችዋም እንባን እጅግ እያፈሰሳችሁ ወዮ በሉ።
እግዚአብሔር የጽዮንን ሴቶች ልጆችና ወንዶች ልጆች እድፍ ያጥባልና፥ በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስም ከመካከላቸው ደምን ያነጻልና።
ዝሙትሽን ከእነርሱ ጋር አበዛሽ፤ ከአንቺ የራቁ ብዙዎችንም ተጐዳኘሽ። መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፤ ከእነርሱም ጋር ተወገድሽ፤ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።
በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃነት አለ፤ ጽሕማቸውን ሁሉ ይላጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ሁሉም በወገባቸው ማቅን ይታጠቃሉ።
ሐሴቦን ሆይ! ጋይ ፈርሳለችና አልቅሽላት፤ እናንተም የራባት ሴቶች ልጆች ሆይ! ሚልኮም፥ ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፤ ማቅም ታጠቁ፤ አልቅሱም።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢየሩሳሌም መሳፍንቱንና ደናግሉን ወደ ምድር አወረዷቸው።
ማቅም ትታጠቃላችሁ፤ ድንጋጤም ይሸፍናችኋል፤ በፊትም ሁሉ ላይ ሐፍረት ይሆናል፤ በራሳችሁም ሁሉ ላይ ቡሃነት ይሆናል።
እኔም እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሀትን፥ ክሳትንም፥ ዐይናችሁንም የሚያፈዝዝ፥ ሰውነታችሁንም የሚያጠፋ ትኩሳት አወርድባችኋለሁ፤ ዘራችሁንም በከንቱ ትዘራላችሁ፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
እግዚአብሔር በክሳት፥ በንዳድም፥ በጥብሳትም፥ በትኵሳትም፥ በድርቅም፥ በዋግም፥ በአረማሞም ይመታሃል፤ እስክትጠፋም ድረስ ያሳድዱሃል።
በራብ ያልቃሉ፤ ለሰማይ ወፎችም መብል ይሆናሉ፤ ኀይላቸውም ይደክማል፥ ከምድር ይጠፉ ዘንድ የምድር አራዊትን ጥርስ፥ ከመርዝ ጋር እልክባቸዋለሁ።
ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።