እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
ኢሳይያስ 1:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታጠቡ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ የሰውነታችሁን ክፋት ከዐይኖች ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግንም ተዉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታጠቡ፤ ራሳችሁንም አንጹ፤ ክፉ ሥራችሁን ከፊቴ አርቁ፤ ክፉ ማድረጋችሁን ተዉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቁንስ ታጥባችሁ ንጹሕ ሁኑ፤ ክፉ ሥራችሁን ሁሉ ከፊቴ አስወግዱ፤ በደል መፈጸማችሁንም ተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታጠቡ ሰውነታችሁንም አንጹ፥ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፥ |
እግዚአብሔርም፥ “ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ለአባቶቻችሁም እንዳዘዝሁት፥ በባሪያዎቼ በነቢያት የላክሁላችሁን ትእዛዜንና ሥርዐቴን፥ ሕጌንም ሁሉ ጠብቁ” ብሎ በነቢዩ ሁሉና በባለ ራእዩ አፍ ሁሉ በእስራኤልና በይሁዳ መሰከረ።
እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።
ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከመጥፎ መንገድ መልስ። እግዚአብሔር የቀኝ መንገዶችን ያውቃልና፥ የግራ መንገዶች ግን ጠማሞች ናቸው። እርሱም መሄጃህን የቀና ያደርጋል፥ አካሄድህንም በሰላም ያሳምራል።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
አሁን እንግዲህ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ክፉ ነገር እፈጥርባችኋለሁ፤ ምክርንም እመክርባችኋለሁ፤ አሁንም ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ መንገዳችሁንና ሥራችሁንም አቅኑ ብለህ ተናገራቸው።”
እርሱም፥ “ሁላችሁ እናንተ ከክፉ መንገዳችሁና ከሥራችሁ ክፋት ተመለሱ፤ እግዚአብሔርም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ትቀመጣላችሁ አለ።
ምናልባት እያንዳንዳቸው ይሰሙ፥ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።”
ደግሞም፦ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፤ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታገለግሉአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፤ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ ባሪያዎችን ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ጆሮአችሁን አላዘነበላችሁም፤ እኔንም አልሰማችሁኝም።
ክፉውን ጥሉ፤ መልካሙንም ውደዱ፤ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፤ ምናልባት ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።
ሰዎችና እንስሶችም ማቅ ይልበሱ፤ ወደ እግዚአብሔርም በአንድነት ይጩኹ፤ ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ከአለው ግፍ ይመለሱ።
ኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞች ገና ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ በምቾትም ተቀምጠው ሳሉ፥ ደቡቡና ቈላውም ሰዎች ባሉባቸው ጊዜ፥ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት እጅ የተናገረውን ቃል መስማት አይገባችሁምን?
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለሆን ራሳችንን እናንጻ፤ ሥጋችንን አናርክስ፤ ነፍሳችንንም አናሳድፍ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት የምንቀደስበትን እንሥራ።