የአሦርም ንጉሥ እስራኤልን ወደ አሦር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር በጎዛንም ወንዝ፥ በሜዶንም አውራጃዎች አኖራቸው፤
ሆሴዕ 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል ተውጦአል፤ በአሕዛብም መካከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤል ተውጠዋል፤ በአሕዛብም መካከል፣ ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤል ተውጦአል፤ አሁን በአሕዛብ መካከል እንደ ረከሰ ዕቃ ሆነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ በአሕዛብ መካከል ተውጠው ቀርተዋል፤ ዋጋ እንደሌለው ዕቃም ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤል ተውጦአል፥ በአሕዛብ መካከል ዛሬ እንደ ረከሰ ዕቃ ሆኖአል። |
የአሦርም ንጉሥ እስራኤልን ወደ አሦር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር በጎዛንም ወንዝ፥ በሜዶንም አውራጃዎች አኖራቸው፤
አወዳደቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደቀቀ ይሆናል፤ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት፥ ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።”
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።
ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ።
ሞአብንም ለምንም እንደማይጠቅም ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞአብ ሰገነት ሁሉ ላይ፥ በአደባባዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግዚአብሔር።
“እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።”
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፤ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፥ “ውጠናታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፤ አግኝተናታል አይተናትማል” ይላሉ።
ቤት። እግዚአብሔር የያዕቆብን መልካም ነገር ሁሉ አሰጠመ፤ አልራራምም፤ በመዓቱ የይሁዳን ሴት ልጅ አንባዎች አፈረሰ፤ ወደ ምድርም አወረዳቸው፤ መንግሥቷንና ግዛቷንም አረከሰ።
ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ።
ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ አዋርደዋችኋልና፤ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የአሕዛብ ማላገጫ ሆናችኋልና፤
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም ኀይሉን የሚገልጽበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ፥ ትዕግሥቱን ካሳየ በኋላ ለማጥፋት የተዘጋጁትን ቍጣውን የሚገልጽባቸውን መላእክት ያመጣል።
“እግዚአብሔር ከጠላቶችህ ፊት የተመታህ ያደርግሃል፤ በአንድ መንገድ ትወጣባቸዋለህ፤ በሰባት መንገድም ከእነርሱ ትሸሻለህ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ የተበተንህ ትሆናለህ።
እግዚአብሔርም ከምድር ዳር እስከ ዳርቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕዛብ ሁሉ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተና አባቶችህ ያላወቃችኋቸውን ሌሎችን አማልክት፥ እንጨትንና ድንጋይን ታመልካለህ።