ከልጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል ሀገር በገባዖን ለእግዚአብሔር እንሠቅላቸዋለን።” ንጉሡም፥ “እሰጣችኋለሁ” አለ።
ሆሴዕ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኮረብታ ላይ መለከትን ንፉ፤ በተራሮችም ላይ ጩኹ፤ ብንያም በተዋረደበት በቤትአዌን ዐዋጅ ንገሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በጊብዓ መለከትን፣ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤ ‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጊብዓ ቀንደ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ “ብንያም ሆይ! ከአንተ ጋር ነን እያላችሁ በቤትአዌን ላይ የማስጠንቀቂያውን ነጋሪት ድምፅ አሰሙ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለጦርነት እንዲወጡ በገባዖን የመለከት፥ በራማም የጥሩንባ ድምፅ አሰሙ! በቤትአዌን “የብንያም ነገድ ሆይ! ከአንተ ጋር ነን” እያላችሁ ጩኹ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጊብዓ መለከትን፥ በራማ እንቢልታን ንፉና፦ ብንያም ሆይ፥ ከአንተ በኋላ እያላችሁ በቤትአዌን ላይ እሪ በሉ። |
ከልጆቹ ሰባት ሰዎች ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል ሀገር በገባዖን ለእግዚአብሔር እንሠቅላቸዋለን።” ንጉሡም፥ “እሰጣችኋለሁ” አለ።
በይሁዳ ዘንድ ተናገሩ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩና፦ በሀገሪቱ ላይ መለከት ንፉ በሉ፤ ጮኻችሁም፦ ሁላችሁ ተሰብሰቡ፤ ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ በሉ።
እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላቅም ጥፋት ከመስዕ ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሸሽ ጽኑ፤ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፤ በቤትካሪም ላይ ምልክትን አንሡ።
የሰማርያ ሰዎች በቤትአዌን እንቦሳ አጠገብ ይኖራሉ፤ ሕዝቡ ያለቅሱለታል፤ ክብሩም ከእርሱ ዘንድ ወጥቶአልና እንዳዘኑበት እንዲሁ በክብሩ ደስ ይላቸዋል።
እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ።
በብብታቸው እንደ መሬት፤ በእግዚአብሔርም ቤት እንደ ንስር ይመጣል። ቃል ኪዳኔን ተላልፈዋልና፥ በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና።
በጽዮን መለከትን ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ ዐዋጅ ንገሩ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይደንግጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?
ኢያሱም ከቤቴል በምሥራቅ በኩል በቤትአዊን አጠገብ ወዳለችው ወደ ጋይ ሰዎችን ከኢያሪኮ ልኮ፥ “ውጡ፤ ጋይንም ሰልሉ” ብሎ ተናገራቸው፤ ሰዎቹም ወጡ፤ ጋይንም ሰለሉ።
በአማሌቅ ዘንድ ሥር የነበራቸው እነርሱ ከኤፍሬም፥ ብንያም ሆይ! በሕዝብ መካከል ከአንተ በኋላ ወረዱ፤ አለቆች ከማኪር፥ የንጉሥንም ዘንግ የሚይዙ ከዛብሎን ወረዱ።
ቤቱም በዚያ ነበረና ወደ አርማቴም ይመለስ ነበር፤ በዚያም በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።