አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ።
ዘፍጥረት 33:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ከተመለሰ በኋላ፣ በከነዓን ወዳለችው ወደ ሴኬም በደኅና ደረሰ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም፥ ከፓዳን-ኣሪም በተመለሰ ጊዜ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው፥ ሴኬም ከተማ በሰላም መጣ፥ እናም በከተማይቱ ፊት ለፊት ሰፈረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ እዚያም በከተማይቱ ፊት ለፊት በሚገኘው ሜዳ ላይ ሰፈረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ከሁለት ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከንዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም ከተማ በደኅንነት መጣ በከተማይቱም ፊት ሰፈረ። |
አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚያች ምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በዚያች ምድር ነበሩ።
ይስሐቅም ሚስት ትሆነው ዘንድ የሶርያዊውን የላባን እኅት፥ የሶርያዊውን የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ከሁለቱ ከሶርያ ወንዞች መካከል በወሰዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።
ተነሣና ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሂድ፤ ከዚያም ከእናትህ ከርብቃ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን አግባ።
ላባም ያዕቆብን አገኘው፤ ያዕቆብም ድንኳኑን በተራራው ላይ ተክሎ ነበር፤ ላባም ወንድሞቹን በገለዓድ ተራራ አስቀመጣቸው።
እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርያ ከተመለሰ በኋላ እንደገና በሎዛ ተገለጠለት፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
እስራኤልም ዮሴፍን፥ “ወንድሞችህ በሴኬም በጎችን የሚጠብቁ አይደሉምን? ወደ እነርሱ እልክህ ዘንድ ና” አለው። እርሱም፥ “እሺ” አለው።
ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።
እኔም ከሶርያ መስጴጦምያ በመጣሁ ጊዜ፥ ወደ ኤፍራታ ለመግባት ጥቂት ቀርቶኝ በፈረስ መጋለቢያው መንገድ ሳለሁ፥ ራሔል በከነዓን ምድር ሞተችብኝ፤ በዚያም በኤፍራታ ወደ ፈረስ መጋለቢያ በሚወስደው መንገድ ላይ ቀበርኋት፤ እርስዋም ቤተ ልሔም ናት።”
ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ።
ዮሐንስም በዮርዳኖስ ማዶ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን ያጠምቅ ነበር፤ በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና፤ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ያጠምቃቸው ነበር።
ኢያሱም የእስራኤልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበሰበ፤ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች፥ አለቆቻቸውንም፥ ጸሓፊዎቻቸውንም፥ ፈራጆቻቸውንም ጠራቸው። በእግዚአብሔርም ፊት አቆማቸው።
የይሩበኣል ልጅ አቤሜሌክም ወደ ሰቂማ ወደ እናቱ ወንድሞች ሄደ፤ ለእነርሱም፥ ለእናቱ አባት ቤተ ሰቦችም ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦