ዘፍጥረት 25:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ሚስት ትሆነው ዘንድ የሶርያዊውን የላባን እኅት፥ የሶርያዊውን የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ከሁለቱ ከሶርያ ወንዞች መካከል በወሰዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅ ርብቃን ሲያገባ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ርብቃ በሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ የሚኖረው የሶርያዊው የባቱኤል ልጅ፣ የሶርያዊውም የላባ እኅት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም አርባ ዓመት ሲሆነው ርብቃን አገባ፥ እርሷም በመስጴጦምያ የሚኖሩ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርያዊው የላባ እኅት ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሚኖሩ ሶርያውያን ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በሁለት ወንዞች መካከል ያለ የሶርያዊው የባቱኤል ልጅና የሶርይዊው የላባ እኅት ናት። |
እንደዚህ በልቡ ያሰበውን መናገሩን ሳይፈጽም እንዲህ ሆነ፦ የአብርሃም ወንድም የናኮር ሚስት የሚልካ ልጅ የባቱኤል ሴት ልጅ ርብቃ እነሆ፥ መጣች፥ እንስራዋንም በጫንቃዋ ተሸክማ ነበር።
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ተነሣና ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሂድ፤ ከዚያም ከእናትህ ከርብቃ ወንድም ከላባ ሴቶች ልጆች ሚስትን አግባ።
መንጎቹንም ሁሉ፥ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁለቱ ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
ያዕቆብም ከሁለቱ ወንዞች መካከል በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሰቂሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከተማዪቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆችም፤ ጋድ፥ አሴር፤ እነዚህ በሁለቱ ወንዞች መካከል በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።
እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከሁለት ወንዞች መካከል ከሶርያ ከተመለሰ በኋላ እንደገና በሎዛ ተገለጠለት፤ እግዚአብሔርም ባረከው።
ልያ በመስጴጦምያ በሶርያ ለያዕቆብ የወለደቻቸው ልጆችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነዚህ ናቸው፤ ወንዶችም ሴቶችም ልጆችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።
በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም ብዙ ለምጻሞች በእስራኤል ውስጥ ነበሩ፤ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነዚያ አንድ እንኳን አልነጻም።”
በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።