Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 24:67 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

67 ይስ​ሐ​ቅም ወደ እናቱ ቤት ገባ፤ ርብ​ቃ​ንም ወሰ​ዳት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወደ​ዳት፤ ይስ​ሐ​ቅም ስለ እናቱ ስለ ሣራ ተጽ​ናና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

67 ይሥሐቅም ርብቃን ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን ይዟት ገባ፤ አገባት፣ ሚስትም ሆነችው፤ እርሱም ወደዳት። ይሥሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

67 ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት፥ ርብቃንም ወሰዳት፥ ሚስትም ሆነችው፥ ወደዳትም፥ ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

67 ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

67 ይስሐቅም ወደ እናቱ ወደ ሣራ ድንኳን አገባት ርብቃንም ወሰዳት ሚስትም ሆነችው ወደዳትም ይስሐቅም ከእናቱ ሞት ተጽናና።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 24:67
16 Referencias Cruzadas  

ዘመ​ን​ዋም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ የይ​ሁዳ ሚስት ሴዋ ሞተች፤ ይሁ​ዳም ተጽ​ናና፤ የበ​ጎ​ቹን ጠጕር ወደ​ሚ​ሸ​ል​ቱት ሰዎ​ችም ወደ ተምና ወጣ፤ እር​ሱም ዓዶ​ሎ​ማ​ዊው በግ ጠባ​ቂው ኤራ​ስም።


ወን​ዶች ልጆ​ቹና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ። ኀዘ​ኑ​ንም ያስ​ተ​ዉት ዘንድ አባ​ታ​ቸ​ውን ማለ​ዱት። ኀዘ​ኑ​ንም መተ​ውን እንቢ አለ፥ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ወደ ልጄ ወደ መቃ​ብር እያ​ዘ​ንሁ እወ​ር​ዳ​ለሁ።” አባ​ቱም ስለ እርሱ አለ​ቀሰ።


በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤


ነገር ግን ወንድሞች ሆይ!ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።


ይዤ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ወላጅ እና​ቴም እል​ፍኝ ባገ​ባ​ሁህ፥ እኔ ከመ​ል​ካሙ የወ​ይን ጠጄ ከሮ​ማ​ኔም ውኃ ባጠ​ጣ​ሁህ ነበር።


ያዕ​ቆ​ብም ራሔ​ልን ወደ​ዳት፤ ያዕ​ቆ​ብም ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ስለ ታና​ሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገ​ዛ​ል​ሃ​ለሁ። ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ እር​ስ​ዋን ስጠኝ” አለው።


ይስ​ሐ​ቅም ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የላ​ባን እኅት፥ የሶ​ር​ያ​ዊ​ውን የባ​ቱ​ኤ​ልን ልጅ ርብ​ቃን ከሁ​ለቱ ከሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል በወ​ሰ​ዳት ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር።


አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ድን​ኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስ​ፈ​ሪያ የተ​ሰ​ለቀ ዱቄት ፈጥ​ነሽ ለውሺ፤ እን​ጎ​ቻም አድ​ርጊ” አላት።


ሎሌ​ውም ያደ​ረ​ገ​ውን ነገር ሁሉ ለይ​ስ​ሐቅ ነገ​ረው።


አብ​ር​ሃ​ምም ደግሞ ስምዋ ኬጡራ የተ​ባ​ለች ሚስት አገባ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios