ዘፍጥረት 25:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው። ርብቃ ዔሳውንና ያዕቆብን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ከዚያም ወንድሙ ተወለደ፤ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ወጣ፤ ከዚህም የተነሣ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ርብቃ ልጆቿን ስትወልድ፣ ይሥሐቅ የስድሳ ዓመት ሰው ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስለዚህ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ልጆቹን በወለደች ጊዜ ይስሐቅ ሥልሳ ዓመት ሆኖት ነበር። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ሁለተኛው ልጅ ሲወለድ የዔሳውን ተረከዝ ይዞ በመውጣቱ ያዕቆብ ተባለ፤ ልጆቹ በተወለዱ ጊዜ ይስሐቅ ሥልሳ ዓመት ሆኖት ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ከዚይም በኍላ ወንድሙ ወጣ በእጁም፥ የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙም ያዕቆብ ተባለ። እርስዋ ልጆችን በወለደቻቸው ጊዜ ይስሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር። Ver Capítulo |