ዘፍጥረት 20:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያች ሌሊትም አቤሜሌክ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር በሕልም ወደ እርሱ መጣ፤ እንዲህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርስዋ ባለ ባል ናትና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም በአንድ ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጥቶ፣ “እነሆ፤ በወሰድሃት ሴት ምክንያት ምዉት ነህ፤ እርሷ ባለባል ናት” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ትሞታለህ፤ እርሷ ባለ ባል ናትና” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ እንዲህም አለው፤ እነሆ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ እርስዋ ባለ ባል ናትና። |
ፈርዖንም አብራምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደረግህብኝ ምንድን ነው? እርስዋ ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልገለጥህልኝም?
አሁንም የሰውየውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፤ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት፥ ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በርግጥ ዕወቅ።”
ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፥ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፥ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበትና ይወርዱበት ነበር።
እግዚአብሔርም ወደ ሶርያዊው ወደ ላባ በሌሊት በሕልም መጥቶ፥ “በባሪያዬ በያዕቆብ ላይ ክፉ ነገር እንዳትናገር ተጠንቀቅ” አለው።
ደግሞም ሌላ ሕልምን አየ፤ ለአባቱና ለወንድሞቹም ነገራቸው፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ደግሞ ሌላ ሕልም አለምሁ፤ ሕልሙም እንዲህ ነው፦ ፀሐይና ጨረቃ ዐሥራ አንድ ከዋክብትም ይሰግዱልኝ ነበር።”
ሁለቱም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለሙ። በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ አበዛዎች አለቃ ሁለቱም እየራሳቸው ሕልምን አለሙ።
እነርሱም፥ “ሕልምን አልመን የሚተረጕምልን አጣን” አሉት። ዮሴፍም አላቸው፥ “ሕልምን የሚተረጕም እግዚአብሔር የሰጠው አይደለምን? እስቲ ንገሩኝ፤ ሕልማችሁ ምንድን ነው?”
ዮናስም የአንድ ቀን መንገድ ያህል ወደ ከተማዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች አለ።”
እርሱ ግን ይህን ሲያስብ፥ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ታየው፤ እንዲህም አለ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተፀነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ።
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።