Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮናስ 3:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮና​ስም የአ​ንድ ቀን መን​ገድ ያህል ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ውስጥ ሊገባ ጀመረ፤ ጮኾም፥ “በሦ​ስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገ​ለ​በ​ጣ​ለች አለ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ዮናስም ወደ ከተማዪቱ ገብቶ የመጀመሪያውን ቀን ከተጓዘ በኋላ “ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ዐወጀ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ዮናስ ወደ ከተማይቱ መግባት ጀመረ፥ የአንድ ቀን መንገድ ያህል እንደ ገባ “አሁንም ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች” ብሎ ጮኸ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ዮናስ ወደ ከተማይቱ ገብቶ ጒዞውን ጀመረ፤ የአንድ ቀን መንገድም እንደ ሄደ “ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትደመሰሳለች!” ብሎ ዐወጀ።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 3:4
10 Referencias Cruzadas  

ያ ነቢይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ከተ​ና​ገ​ረው ሁሉ ቃሉ ባይ​ደ​ርስ፤ እንደ ተና​ገ​ረ​ውም ባይ​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያን ቃል አል​ተ​ና​ገ​ረ​ውም፤ ነቢዩ በሐ​ሰት ተና​ግ​ሮ​ታ​ልና አት​ስ​ማው።


እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ ከተናገረው ክፉ ነገር ተመለሰ፤ አላደረገውምም።


በዕ​ድ​ሜ​ህም ላይ ዐሥራ አም​ስት ዓመት እጨ​ም​ራ​ለሁ፤ አን​ተ​ንና ይህ​ችን ከተማ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ እታ​ደ​ጋ​ለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪ​ያ​ዬም ስለ ዳዊት ይህ​ችን ከተማ አጋ​ር​ዳ​ታ​ለሁ።”


በዚ​ያም ወራት ሕዝ​ቅ​ያስ ታመመ፤ ለሞ​ትም ደረሰ። ነቢ​ዩም የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ትሞ​ታ​ለህ እንጂ በሕ​ይ​ወት አት​ኖ​ር​ምና ቤት​ህን አስ​ተ​ካ​ክል” አለው።


የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።


ዮናስ ለነ​ነዌ ሰዎች ምል​ክት እንደ ሆና​ቸው የሰው ልጅም ለዚች ትው​ልድ እን​ዲሁ ምል​ክት ይሆ​ና​ታል።


የነ​ነዌ ሰዎች በፍ​ርድ ቀን ከዚች ትው​ልድ ጋር ተነ​ሥ​ተው ይፋ​ረ​ዱ​አ​ታል፤ ያሳ​ፍ​ሩ​አ​ታ​ልም፤ ዮናስ በሰ​በ​ከ​ላ​ቸው ጊዜ ንስሓ ገብ​ተ​ዋ​ልና፤ እነሆ፥ ከዮ​ናስ የሚ​በ​ልጥ በዚህ አለ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራጅ ነውና ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይራ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ ይታ​ገ​ሣል፤ ይም​ራ​ች​ሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እር​ሱን በመ​ተ​ማ​መን የሚ​ጠ​ባ​በቁ ሁሉ ብፁ​ዓን ናቸው።


አደ​ር​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከአ​ሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር ተመ​ል​ሻ​ለ​ሁና በዚች ምድር ብት​ቀ​መጡ እሠ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ች​ሁም፥ እተ​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ች​ሁም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios