ዕዝራ 2:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናታኒም፤ የሲሓ ልጆች፥ የሐሡፊ ልጆች፥ የጠብዖት ልጆች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ የጠብዖት ዘሮች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ የፂሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣባዖት ልጆች አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለቤተ መቅደስ ሥራ ከተመደቡትም መካከል ከምርኮ የተመለሱት ጐሣዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ጺሐ፥ ሐሱፋ፥ ጣባዖት፥ ቄሮስ፥ ሲዓሃ፥ ፋዶን፥ ለባና፥ ሐጋባ፥ ዓቁብ፥ ሐጋብ፥ ሻምላይ፥ ሐናን፥ ጊዴል፥ ጋሐር፥ ረአያ፥ ረጺን፥ ነቆዳ፥ ጋዛም፥ ዑዛ፥ ፓሴሐ፥ ቤሳይ፥ አስና፥ መዑኒም፥ ነፊሲም፥ ባቅቡቅ፥ ሐቁፋ፥ ሐርሑር፥ ባጽሉት፥ መሒዳ፥ ሐርሻ፥ ባርቆስ፥ ሲሣራ ቴማሕ፥ ነጺሐና ሐጢፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናታኒም፤ የሲሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ |
የበረኞች ልጆች፥ የሰሎም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጤልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሰበዋይ ልጆች ሁሉ መቶ ሠላሳ ዘጠኝ።
ከእስራኤልም ልጆች ከካህናቱም፥ ከሌዋውያኑም፥ ከመዘምራኑም፥ ከበረኞቹም፥ ከናታኒምም በንጉሡ በአርተሰስታ በሰባተኛው ዓመት ዐያሌዎች ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ።
በካሲፍያ ስፍራ ወደ ነበረው ወደ አለቃው ወደ አዶ ላክኋቸው፤ ለአምላካችን ቤትም አገልጋዮችን ያመጡልን ዘንድ በካሲፍያ ስፍራ ለሚኖሩት ለአዶና ለወንድሞቹ ለናታኒም የሚነግሩአቸውን በአፋቸው አደረግሁ።
ሌዋውያንንም እንዲያገለግሉ ዳዊትና አለቆቹ ከሰጡአቸው ናታኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታኒምን አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በስም በስማቸው ተሰበሰቡ።
የቀሩትም ሕዝብ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ በረኞቹም፥ መዘምራንም፥ ናታኒምም፥ ከምድርም አሕዛብ ራሳቸውን የለዩና ወደ እግዚአብሔር ሕግ የገቡ ሁሉ፥ ሚስቶቻቸውም፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም፥ የሚያውቁትና የሚያስተውሉትም ሁሉ ወንድሞቻቸውንና ታላላቆቻቸውን አበረታቱ፤
በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የሀገሩ አለቆች እነዚህ ናችው፤ እስራኤል ግን ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ ናታኒምም፥ የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ።
ሌዋውያንንም ወደ ወንድምህ ወደ አሮንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህናቱ ታገባቸዋለህ። ከእስራኤል ልጆች ተለይተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰጥተዋልና።