ዕዝራ 10:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤላም ልጆች ወገን የነበረውም የኢያሔል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “አምላካችንን በድለናል፤ የምድርንም አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ከኤላም ዘሮች አንዱ የሆነው የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፤ “በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ፣ ባዕዳን ሴቶችን በማግባታችን ለአምላካችን ታማኞች ሆነን አልተገኘንም፤ ይህም ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዔላም ልጆች ወገን የነበረ፥ የይሒኤል ልጅ ሽካንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለአምላካችን ታማኞች አልሆንም፥ የምድሪቱን ሕዝቦች እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፥ አሁንም ግን በዚህ ነገር ለእስራኤል ተስፋ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ከዔላም ጐሣ የየሒኤል ልጅ ሸካንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ እኛ በአካባቢአችን ካሉት አሕዛብ ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በእግዚአብሔር ላይ የነበረንን እምነት አጓድለናል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኤላም ልጆች ወገን የነበረ የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “አምላካችንን በድለናል፤ የምድርን አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ። |
ይህም ከተፈጸመ በኋላ የሕዝቡ አለቆች ወደ እኔ ቀርበው፥ “የእስራኤል ሕዝብ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ እንደ ከነዓናውያን፥ እንደ ኬጤዎናውያን፥ እንደ ፌርዜዎናውያን፦ እንደ ኢያቡሴዎናውያን፥ እንደ አሞናውያን፥ እንደ ሞዓባውያን፥ እንደ ግብፃውያንና እንደ አሞራውያን ርኵሰት ያደርጋሉ እንጂ ከምድር አሕዛብ አልተለዩም፤
ለራሳቸውና ለልጆቻቸውም ሴቶች ልጆቻቸውን ወስደዋል፤ የተቀደሰውንም ዘር ከምድር አሕዛብ ጋር ደባልቀዋል፤ አስቀድሞም አለቆቹና ሹሞቹ በዚህ መተላለፍ መጀመሪያ ሆነዋል” አሉኝ።
እንዲሁ እንግዲህ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት ስትሠሩ፥ እንግዶችንም ሴቶች በማግባት አምላካችንን ስትበድሉ አንስማባችሁ።”
ከዚያም በኋላ የሄሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አንጻር ያለውን ሠራ። ከእርሱም በኋላ የምሥራቁ በር ጠባቂ የሴኬንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።
በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባበት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤