Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 10:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚህም በኋላ ከዔላም ጐሣ የየሒኤል ልጅ ሸካንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፦ “በእርግጥ እኛ በአካባቢአችን ካሉት አሕዛብ ባዕዳን ሴቶችን በማግባት በእግዚአብሔር ላይ የነበረንን እምነት አጓድለናል፤ ይህም ሁሉ ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ከኤላም ዘሮች አንዱ የሆነው የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ አለው፤ “በዙሪያችን ካሉት አሕዛብ፣ ባዕዳን ሴቶችን በማግባታችን ለአምላካችን ታማኞች ሆነን አልተገኘንም፤ ይህም ሆኖ አሁንም ለእስራኤል ተስፋ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከዔላም ልጆች ወገን የነበረ፥ የይሒኤል ልጅ ሽካንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለአምላካችን ታማኞች አልሆንም፥ የምድሪቱን ሕዝቦች እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፥ አሁንም ግን በዚህ ነገር ለእስራኤል ተስፋ አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከኤ​ላም ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውም የኢ​ያ​ሔል ልጅ ሴኬ​ንያ ዕዝ​ራን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን በድ​ለ​ናል፤ የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ እን​ግ​ዶች ሴቶ​ችን አግ​ብ​ተ​ናል፤ አሁን ግን ስለ​ዚህ ነገር ገና ለእ​ስ​ራ​ኤል ተስፋ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ከኤላም ልጆች ወገን የነበረ የይሒኤል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “አምላካችንን በድለናል፤ የምድርን አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 10:2
17 Referencias Cruzadas  

ከዔላም ጐሣ፦ ማታንያ፥ ዘካርያስ የሒኤል፥ ዐብዲ፥ የሬሞትና ኤልያ፤


ይህም ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ መሪዎች አንዳንዶቹ ወደ እኔ ቀርበው ከዚህ የሚከተለውን ቃል ነገሩኝ፦ “ሕዝቡና ካህናቱ ሌዋውያኑም ጭምር በጐረቤት ባሉት በዐሞን፥ በሞአብና በግብጽ ከሚኖሩትና እንዲሁም ከከነዓናውያን፥ ከሒታውያን፥ ከፈሪዛውያን፥ ከኢያቡሳውያንና ከአሞራውያን ርኲሰት ራሳቸውን አልጠበቁም፤ እነዚያ አሕዛብ ሲፈጽሙት የነበረውን አጸያፊ ነገር ሁሉ አድርገዋል።


ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።”


ታዲያ እኛስ የእናንተን ምሳሌነት መከተልና የባዕዳን አገሮች ሴቶችን በማግባት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መተላለፍ ይገባናልን?”


የኢሜር ልጅ ሳዶቅ በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ሲሠራ የምሥራቅ ቅጽር በር ጠባቂው የሸካንያ ልጅ ሸማዕያ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ሠራ።


አጥፊ ወጥመድ ስለሚሆኑባችሁ ከምትሄዱባቸው ሕዝቦች ጋር ቃል ኪዳን አትግቡ።


ኃጢአቱን የሚደብቅ ኑሮው አይሳካለትም፤ ኃጢአቱን ተናዝዞ ዳግመኛ ኃጢአት ከመሥራት የሚቈጠብ ግን የእግዚአብሔርን ምሕረት ያገኛል።


በሰዎች መካከል ልዩነት ብታደርጉ ግን ኃጢአት ትሠራላችሁ፤ ሕግን በመተላለፋችሁም ትወቀሳላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos