የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
ዘፀአት 31:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ ሁለቱን የምስክር ጽላት፥ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ መናገሩን ከፈጸመ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት፣ ሁለቱን የምስክር ጽላት ለርሱ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች የሆኑ ሁለት የምስክር ጽላቶችን ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው። |
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፤ በዚያም ሁን፤ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ፥ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ፤ ሕግንም ትሠራላቸዋለህ” አለው።
ጠንቋዮችም ፈርዖንን፥ “ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈርዖን ልብ ግን ጸና፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።
ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
እኔ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆነ እንግዲህ አሁን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።
እናንተ ራሳችሁም በእኛ የተላከች የክርስቶስ መልእክት እንደ ሆናችሁ ያውቃሉ፤ ይህቺውም የተጻፈች በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ ነው እንጂ በቀለም አይደለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌዳነት ነው እንጂ በድንጋይ ሠሌዳም አይደለም።
እግዚአብሔርም በተራራው ላይ በእሳት መካከል የተናገራችሁን ዐሠርቱን ቃላት ቀድሞ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቱ ላይ ጻፈ፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።
“እግዚአብሔር በተራራው ላይ፤ በእሳትና በጨለማ፥ በጭጋግና በዓውሎ ነፋስ መካከል ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤያችሁ ሁሉ ተናገረ፤ ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላት ላይ ጻፋቸው፤ ለእኔም ሰጣቸው።
በውስጥዋም የወርቅ ማዕጠንትና ሁለንተናዋን በወርቅ የለበጡአት፥ የኪዳን ታቦት፥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የለመለመችው የአሮን በትር፥ የኪዳኑም ጽላት ነበሩባት።