Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 5:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ፤ በእ​ሳ​ትና በጨ​ለማ፥ በጭ​ጋ​ግና በዓ​ውሎ ነፋስ መካ​ከል ሆኖ በታ​ላቅ ድምፅ እነ​ዚ​ህን ቃሎች ለጉ​ባ​ኤ​ያ​ችሁ ሁሉ ተና​ገረ፤ ምንም አል​ጨ​መ​ረም። በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው፤ ለእ​ኔም ሰጣ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳቱ፣ በደመናውና በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ለማኅበራችሁ ሁሉ በከፍተኛ ድምፅ የተናገራችሁ ትእዛዞቹ እነዚህ ናቸው፤ የጨመረውም ሌላ የለም፤ ትእዛዞቹንም በሁለት የድንጋይ ጽላት ላይ ጽፎ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “እነዚህን ቃሎች ጌታ በተራራው ላይ ለጉባኤአችሁ ሁሉ በእሳትና በደመና፥ በድቅድቅ ጨለማው ውስጥ ሆኖ፥ በታላቅ ድምፅ ተናገረ፥ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 “በተሰበሰባችሁ ጊዜ እግዚአብሔር በተራራው ላይ ሆኖ ለእናንተ ለሁላችሁም የሰጣችሁ ትእዛዞች እነዚህ ናቸው፤ በእሳት፥ በደመናና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ብርቱ በሆነ ታላቅ ድምፅ በተናገረ ጊዜ የሰጣችሁ ትእዛዞች እነዚህ ብቻ ናቸው። እነርሱንም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጽፎ ለእኔ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመናው በጨለማውም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ተናገረ፤ ምንም ምን አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው፥ ለእኔም ሰጣቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 5:22
11 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለፊት ተና​ገ​ራ​ችሁ።


ያስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ከሰ​ማይ ድም​ፁን አሰ​ማህ፤ በም​ድ​ርም ላይ ታላ​ቁን እሳት አሳ​የህ፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ቃሉን ሰማህ።


ሊዳ​ሰስ ወደ​ሚ​ችል ወደ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም እሳት ወደ ጭጋ​ግም፥ ወደ ጨለ​ማም ወደ ዐውሎ ነፋ​ስም፥


ሕዝ​ቡም ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለ​በት ወደ ጨለ​ማው ቀረበ።


“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በእ​ሳት መካ​ከል ድም​ፁን በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ሲነ​ድድ እና​ንተ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ወደ እኔ ቀረ​ባ​ችሁ፤


አንተ ከእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ እንደ ሰማ​ህና በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥


የጻ​ፈ​ላ​ች​ሁ​ንም ሥር​ዐ​ትና ፍርድ፥ ሕግና ትእ​ዛ​ዝም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አት​ፍሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios