Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ቆሮንቶስ 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ስለ ደቀ መዛ​ሙ​ርት

1 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?

2 የእ​ኛስ መጽ​ሐ​ፋ​ችን እና​ንተ ናችሁ፤ በል​ባ​ችን ውስ​ጥም ተጽ​ፋ​ች​ኋል፤ ትታ​ወ​ቃ​ላ​ች​ሁም፤ ሰውም ሁሉ ያነ​ብ​ባ​ች​ኋል።

3 እና​ንተ ራሳ​ች​ሁም በእኛ የተ​ላ​ከች የክ​ር​ስ​ቶስ መል​እ​ክት እንደ ሆና​ችሁ ያው​ቃሉ፤ ይህ​ቺ​ውም የተ​ጻ​ፈች በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው እንጂ በቀ​ለም አይ​ደ​ለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌ​ዳ​ነት ነው እንጂ በድ​ን​ጋይ ሠሌ​ዳም አይ​ደ​ለም።

4 ነገር ግን በክ​ር​ስ​ቶስ በኩል በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እን​ዲህ ያለ እም​ነት አለን።

5 ኀይ​ላ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራ​ሳ​ችን እንደ ሆነ አድ​ር​ገን ምንም ልና​ስብ አይ​ገ​ባ​ንም።

6 በመ​ን​ፈስ እንጂ በፊ​ደል ለማ​ይ​ሆን ለአ​ዲስ ሕግ አገ​ል​ጋ​ዮች አደ​ረ​ገን፤ ፊደል ይገ​ድ​ላል፥ መን​ፈስ ግን ሕያው ያደ​ር​ጋል።


ስለ መል​እ​ክ​ታት መበ​ላ​ለጥ

7 ስለ​ዚያ ስለ አለ​ፈው የፊቱ ብር​ሃን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የሙ​ሴን ፊት መመ​ል​ከት እስ​ኪ​ሳ​ና​ቸው ድረስ በዚ​ያች በድ​ን​ጋይ ላይ በፊ​ደል ለተ​ቀ​ረ​ጸች ለሞት መል​እ​ክት ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት፥

8 ለመ​ን​ፈስ ቅዱስ መል​እ​ክ​ትማ ምንኛ እጅግ ክብር ሊደ​ረግ ይገባ ይሆን?

9 ኵነ​ኔን ለም​ታ​መጣ መል​እ​ክት ብዙ ክብር ከተ​ደ​ረ​ገ​ላት የጽ​ድቅ መል​እ​ክ​ትማ ምን ያህል ትከ​ብ​ርና ትመ​ሰ​ገን ይሆን?

10 በዚህ ፍጹም ክብር ባነ​ጻ​ጸ​ሯት ጊዜ የከ​በ​ረ​ችው እን​ዳ​ል​ከ​በ​ረች ትሆ​ና​ለ​ችና።

11 ያ የሚ​ያ​ል​ፈው ክብር ካገኘ፥ ያ ጸንቶ የሚ​ኖ​ረ​ውማ እን​ዴት እጅግ ክብር ያገኝ ይሆን?

12 እን​ግ​ዲህ ይህን ያህል ተስፋ ካለን በግ​ልጥ ፊት ለፊት ልን​ቀ​ርብ እን​ች​ላ​ለን።

13 የዚ​ያን ይሻር የነ​በ​ረ​ውን መጨ​ረሻ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዳ​ያ​ዩት ፊቱን ይሸ​ፍን እንደ ነበ​ረው እንደ ሙሴ አይ​ደ​ለም።

14 ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ ልባ​ቸው ተሸ​ፍ​ኖ​አል፤ ያም መጋ​ረጃ ብሉይ ኪዳን በተ​ነ​በ​በት ዘመን ሁሉ ጸንቶ ኖሮ​አል፤ ክር​ስ​ቶስ እስ​ኪ​ያ​ሳ​ል​ፈው ድረስ አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ምና።

15 እስከ ዛሬም የሙ​ሴን ሕግ ሲያ​ነ​ብቡ ያ መጋ​ረጃ ልባ​ቸ​ውን ይሸ​ፍ​ና​ቸ​ዋል።

16 ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለሱ ጊዜ ግን ያ መጋ​ረጃ ከእ​ነ​ርሱ ይር​ቃል።

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነውና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ባለ​በ​ትም በዚያ ነፃ​ነት አለ።

18 እኛስ ሁላ​ችን ፊታ​ች​ንን ገል​ጠን በመ​ስ​ተ​ዋት እን​ደ​ሚ​ያይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እና​ያ​ለን፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ እንደ ተሰ​ጠን መጠን የእ​ር​ሱን አር​አያ እን​መ​ስል ዘንድ ከክ​ብር ወደ ክብር እን​ገ​ባ​ለን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos