ዘፀአት 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቂጣውን በዓል ጠብቁ፤ በአዲስ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝኋችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የቂጣ በዓልን አክብር፤ እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን እርሾ የሌለውን ቂጣ ብላ፤ ይህንም በአቢብ ወር በተወሰነ ቀን አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና። “ማንም በፊቴ ባዶ እጁን አይቅረብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ በወጣችሁበት በአቢብ ወር፥ እኔ ባዘዝኳችሁ አኳኋን የቂጣን በዓል አክብሩ፤ ይህ በዓል በሚከበርባቸው በሰባቱ ቀኖች ውስጥ እርሾ የነካው እንጀራ አትብሉ፤ ለእኔ ልትሰግዱ በምትመጡበት ጊዜ መባ ሳትይዙ አትምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በአቢብ ወር ከግብፅ ምድር ወጥታችኋልና በዚህ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላለህ፤ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ። |
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
“የቂጣውን በዓል ትጠብቀዋለህ። በሚያዝያ ወር ከግብፅ ወጥተሃልና በታዘዘው ዘመን በሚያዝያ ወር እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።
የአህያውንም በኵር በበግ ትዋጀዋለህ፤ ባትዋጀው ግን ዋጋውን ትሰጣለህ። የልጆችህንም በኵር ሁሉ ትዋጃለህ። በፊቴም ባዶ እጅህን አትታይ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ፥ መከሩንም ባጨዳችሁ ጊዜ፥ የእናንተን መከር በኵራት ነዶ ወደ ካህኑ አምጡ፤
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤
እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳኑን ታቦት ብትሰድዱአት ስለ አሳዘናችሁአት የበደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶዋን አትስደዱአት፤ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፤ ስርየትም ይደረግላችኋል፤ አለዚያ ግን የእግዚአብሔር እጅ ከእናንተ አይርቅም” አሉ።