ዘፀአት 21:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕብራዊ ባሪያ የገዛህ እንደ ሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፤ በሰባተኛውም ዓመት በነጻ አርነት ይውጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕብራዊ አገልጋይ ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፤ በሰባተኛው ዓመት ግን ያለ ምንም ክፍያ በነጻ ይሂድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕብራዊ ባርያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛው ዓመት ግን እንዲሁ ነፃ ይውጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕብራዊ ባሪያ ብትገዛ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፤ በሰባተኛው ዓመት ያለ ምንም ዕዳ ነጻ እንዲወጣ አድርገው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕብራዊ ባሪያ የገዛህ እንደሆነ ስድስት ዓመት ያገልግልህ፥ በሰባተኛውም በከንቱ አርነት ይውጣ። |
ዔሳውም አለ፥ “በእውነት ስሙ ያዕቆብ ተባለ፤ ሁለት ጊዜ አሰናክሎኛልና፤ መጀመሪያ ብኵርናዬን ወሰደ፤ አሁንም እነሆ በረከቴን ወሰደ።” ዔሳውም አባቱን አለው፥ “ደግሞም አባቴ ሆይ፥ ለእኔ በረከትን አላስቀረህልኝምን?”
ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
እኔም፥ “ለአሕዛብ የተሸጡትን ወንድሞቻችንን አይሁድን በፈቃዳችን ተቤዠን፤ እናንተስ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁን? እነርሱስ ለእኛ የተሸጡ ይሆናሉን?” አልኋቸው። እነርሱም ዝም አሉ፤ መልስም አላገኙም።
እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አያስጨንቅህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።