Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “በፊ​ታ​ቸው የም​ታ​ደ​ር​ገው ሥር​ዐት ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “በፊታቸው የምትደነግጋቸው ሥርዐቶች እነዚህ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “በፊታቸው የምታኖረው ሥርዓት ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “ለእስራኤላውያን የምትሰጣቸው ሕግ ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በፊታቸው የምታደርገው ሥርዓት ይህ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 21:1
27 Referencias Cruzadas  

ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር የም​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ አስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚ​ያን ጊዜ አዘ​ዘኝ።


“ነገ ልጅህ፦ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድስ ምን​ድን ነው? ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ፥


እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።


ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።


ደግ​ሞም መል​ካም ያል​ሆ​ነ​ውን ሥር​ዐት፥ በሕ​ይ​ወት የማ​ይ​ኖ​ሩ​በ​ት​ንም ፍርድ ሰጠ​ኋ​ቸው።


ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ትን ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴ​ንም አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባሪያ በሙሴ እጅ በተ​ሰ​ጠው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሄዱ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ሁሉ፥ ፍር​ዱ​ንም፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ርግ​ማ​ን​ንና መሐ​ላን አደ​ረጉ።


በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ከተ​ቀ​መ​ጡት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በደ​ምና በደም መካ​ከል፥ በሕ​ግና በት​እ​ዛዝ፥ በሥ​ር​ዐ​ትና በፍ​ር​ድም መካ​ከል ያለ ማና​ቸ​ውም ሰው ለፍ​ርድ ወደ እና​ንተ ቢመጣ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ይ​በ​ድሉ፥ ቍጣም በእ​ና​ን​ተና በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ እን​ዳ​ይ​መጣ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቁ​አ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም ብታ​ደ​ርጉ በደ​ለ​ኞች አት​ሆ​ኑም።


“ስለ​ዚህ ስለ​ም​ት​ሠ​ራ​ልኝ ቤት በሥ​ር​ዐቴ ብት​ሄድ፥ ፍር​ዴ​ንም ብታ​ደ​ርግ፥ ትመ​ላ​ለ​ስ​ባ​ቸ​ውም ዘንድ ትእ​ዛ​ዞቼን ሁሉ ብት​ጠ​ብቅ፥ ለአ​ባ​ትህ ለዳ​ዊት የነ​ገ​ር​ሁ​ትን ቃል ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።


“ልት​ወ​ር​ሱ​አት በም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ታደ​ር​ጉት ዘንድ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ያዘ​ዘው ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።


አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድ​ርጌ በም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ላይ ያደ​ር​ጉ​አት ዘንድ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


ሙሴም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ጠርቶ አላ​ቸው፥ “እስ​ራ​ኤል ሆይ እን​ድ​ት​ማ​ሩ​አ​ትም፥ በማ​ድ​ረ​ግም እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቁ​አት ዛሬ በጆ​ሮ​አ​ችሁ የም​ና​ገ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ሙሴ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የተ​ና​ገ​ረው ምስ​ክ​ርና ሥር​ዐት፤ ፍር​ድም ይህ ነው።


ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ እን​ደ​ማ​ኖ​ራት እን​ደ​ዚ​ህች ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆ​ነች ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ያለው ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?


እነሆ፥ እና​ንተ ገብ​ታ​ችሁ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ውስጥ እን​ዲህ ታደ​ርጉ ዘንድ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሥር​ዐ​ትና ፍር​ድን አሳ​የ​ኋ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ እጅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ አጠ​ገብ በኢ​ያ​ሪኮ አን​ጻር በሞ​ዓብ ምዕ​ራብ ያዘ​ዛ​ቸው ትእ​ዛዝ፥ ሥር​ዐ​ትና ፍርድ እነ​ዚህ ናቸው።


ጠላ​ቱም ባይ​ሆን፥ ክፉም ያደ​ር​ግ​በት ዘንድ ባይሻ፥ ማኅ​በሩ በመ​ቺ​ውና በባለ ደሙ መካ​ከል ፍር​ድን እን​ደ​ዚህ ይፍ​ረዱ፤


“እን​ግ​ዲህ ትቀ​መ​ጡ​ባት ዘንድ የማ​ገ​ባ​ችሁ ምድር እን​ዳ​ት​ተ​ፋ​ችሁ ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም።


ሕጌን ሁሉ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እና​ን​ተም የሀ​ገሩ ልጆች፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል የሚ​ኖ​ሩት እን​ግ​ዶች ከዚህ ርኵ​ሰት ምንም አት​ሥሩ፤


የሚ​ሠ​ራ​ቸው ሰው በእ​ነ​ርሱ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልና ሥር​ዐ​ቴ​ንና ፍር​ዴን ጠብቁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ።


ሙሴም መጣ፤ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ይህን ቃል ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ተና​ገረ።


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን ዕብ​ራ​ዊ​ዉን ወይም ዕብ​ራ​ዊ​ቱን ብት​ገዛ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ሉህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከአ​ንተ ዘንድ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ልቀ​ቀው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios