ዘፀአት 12:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፤ እንዲህም አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንደ አዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፥ እንዲሁም አደረጉ፤ ጌታ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሄደውም በሙሴና በአሮን አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፤ እንዲሁም አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ። |
‘ይህ በግብፅ ሀገር የእስራኤልን ልጆች ቤቶች ሰውሮ ግብፃውያንን በመታ ጊዜ፥ ቤቶቻችንን የአዳነ የእግዚአብሔር የፋሲካው መሥዋዕት ነው’ ትሉአቸዋላችሁ።” ሕዝቡም ተጐነበሱ፤ ሰገዱም።
እንዲህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በዙፋን ከተቀመጠው ከፈርዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምርኮኛ በኵር ድረስ፥ በግብፅ ምድር በኵሩን ሁሉ፥ የእንስሳውንም በኵር ሁሉ መታ።
እኔም የፈርዖንን ልብ አጸናለሁ፤ እርሱም ከኋላቸው ይከተላቸዋል፤ እኔም በፈርዖንና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ እከብራለሁ፤ ግብፃውያንም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” እነርሱም እንዲሁ አደረጉ።
“ባስልኤልና ኤልያብ፥ ለመቅደስም ማገልገያ ሥራ ሁሉ ያደርጉ ዘንድ እንዲያውቁ እግዚአብሔር ጥበብንና ማስተዋልን የሰጣቸው በልባቸውም ጥበበኞች የሆኑ ሁሉ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ አደረጉ።”
እንዲሁም የምስክሩ ድንኳን ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ የእስራኤል ልጆች አደረጉ፤ እንዲሁ አደረጉ።
ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፤ እነሆም፥ አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።
ሙሴና አሮንም ወደ ፈርዖን ገቡ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ጣለ፤ እባብም ሆነች።
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ ተሳዳቢውንም ከሰፈር ወደ ውጭ አወጡት፤ በድንጋይም ወገሩት። የእስራኤልም ልጆች እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
ሙሴ ከእስራኤል ልጆች ድርሻ ከሰውና ከእንስሳ ከሃምሳ አንድ ወሰደ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ሌዋውያን ሰጠ።
የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ።
ሙሴም እጆቹን ስለ ጫነበት የነዌ ልጅ ኢያሱ የጥበብን መንፈስ ተሞላ፤ የእስራኤልም ልጆች ታዘዙለት፤ እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።
እርስዋም፥ “እንደ ቃላችሁ ይሁን” አለች፤ አሰናበተቻቸውም፤ እነርሱም ሄዱ፤ ቀዩንም ፈትል በመስኮቱ በኩል አንጠለጠለችው።
የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ የእስራኤልም ልጆች ዮርዳኖስን አካትተው በተሻገሩ ጊዜ እግዚአብሔር ኢያሱን እንደ አዘዘው በእስራኤል ነገድ ቍጥር ከዮርዳኖስ መካከል ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደ ሰፈራቸው ወሰዱ፤ በዚያም አኖሩአቸው።