Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 12:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ሄደውም በሙሴና በአሮን አማካይነት እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፥ እንዲሁም አደረጉ፤ ጌታ ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 የእስራኤልም ልጆች ሄዱ፤ እንዲሁም አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 12:28
23 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጥኤማውያንንም አሸነፈ፤ ከጌባዕ አንሥቶ እስከ ጌዜር ድረስም አባረራቸው።


ኤልያስም እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ሄዶ በከሪት ሸለቆ ተቀመጠ፤


እናንተም እንዲህ ብላችሁ ትመልሱላቸዋላችሁ፤ ‘ይህ እግዚአብሔርን ለማክበር የሚደረግ የፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ እግዚአብሔር በግብጽ ምድር የእስራኤላውያንን መኖሪያ ቤቶች አልፎ በመሄድ ግብጻውያንን ሲገድል እኛን አድኖናል።’ ” እስራኤላውያንም ይህን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ፤


እኩለ ሌሊት ሲሆን እግዚአብሔር ከንጉሡ አልጋ ወራሽ ጀምሮ ከምድር በታች ባለ እስር ቤት ውስጥ እስከ ተጣለው የእስረኛ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ በሞት ቀጣ፤ በኲር ሆነው የተወለዱ እንስሶችም ተገደሉ።


እስራኤላውያን ሙሴ እንዳዘዛቸውም አደረጉ፤ ይኸውም የወርቅና የብር ጌጣጌጥ እንዲሁም ልብስ እንዲሰጡአቸው ግብጻውያንን ጠየቁ።


እኔም ልቡን ስለማደነድነው ያሳድዳችኋል፤ ስለዚህም በንጉሡና በሠራዊቱ ላይ የምጐናጸፈው ድል ለእኔ ክብር ይሆናል፤ በዚያን ጊዜ ግብጻውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።” እስራኤላውያንም እንደ ተነገራቸው አደረጉ።


“ባጽልኤልና ኦሆሊአብ እንዲሁም ለተቀደሰው ድንኳን ዝግጅት እግዚአብሔር ማናቸውንም ሥራ ለመሥራት ችሎታንና ዕውቀትን የሰጣቸው ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ይሠራሉ።”


በመጨረሻም የመገናኛው ድንኳን አሠራር በሙሉ ተፈጸመ፤ እስራኤላውያን ሁሉን ነገር እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤


እስራኤላውያን ሥራውን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሠሩ፤


ሙሴም ሁሉን ነገር መርምሮ ልክ እግዚአብሔር ባለው መሠረት መሥራታቸውን አረጋገጠ፤ ስለዚህም ሙሴ ባረካቸው።


ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በጣለው ጊዜ ተለውጦ እባብ ሆነ።


ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ ፈጸሙ።


ሙሴም ይህን ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ ያን ሰው ከሰፈር አወጡና በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ በዚህም ዐይነት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አደረጉ።


ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሁሉን ነገር አደረጉ።


ሙሴና አልዓዛርም እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ አደረጉ።


ስለዚህም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት መባውን ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግ ለአልዓዛር ሰጠው።


ከዚህም ድርሻ ሙሴ ከኀምሳው አንድ እስረኛ፥ ከኀምሳው አንድ እንስሳ ወስዶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ድንኳን ላይ ኀላፊነት ላላቸው ለሌዋውያን ሰጠ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እስራኤላውያን ከሰፈሩ አስወጡአቸው።


ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።


የበኲር ልጆችን ለመግደል የታዘዘው መልአክ የእስራኤላውያንን የበኲር ልጆች እንዳይገድል በማለት ሙሴ የፋሲካና የደም መርጨትን ሥርዓት ያደረገው በእምነት ነው።


እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት እስራኤላውያን ምድሪቱን ተካፈሉ።


እርስዋም በዚህ ተስማምታ ሸኘቻቸው፤ እነርሱም ከሄዱ በኋላ ቀዩን ገመድ በመስኮቱ ላይ አንጠለጠለች።


ሰዎቹም ኢያሱ እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ እግዚአብሔር ለኢያሱ በነገረው መሠረት በእስራኤል ነገዶች ቊጥር ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ዐሥራ ሁለቱን ድንጋዮች ወደ ሰፈሩበት ቦታ ወስደው አስቀመጡ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos