Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 39:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በዚህ መሠረት የማደሪያው ድንኳን፣ የመገናኛው ድንኳን ሥራ በሙሉ ተጠናቀቀ። እስራኤላውያን ልክ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉን ነገር ሠሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 የመገናኛው ድንኳን የማደሪያው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ። የእስራኤልም ልጆች ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ልክ እንደዛው አድርገው ሠሩ፤ እንዲሁ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በመጨረሻም የመገናኛው ድንኳን አሠራር በሙሉ ተፈጸመ፤ እስራኤላውያን ሁሉን ነገር እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረጉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 እንዲሁም የመገናኛው ድንኳን የማደሪያውም ሥራ ሁሉ ተጨረሰ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ የእስራኤል ልጆች አደረጉ፤ እንዲሁ አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 39:32
24 Referencias Cruzadas  

በተ​ራራ ላይ እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ድ​ት​ሠራ ተጠ​ን​ቀቅ።


እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና።


ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታ​መነ እንደ ሆነ፥ እርሱ ለላ​ከው የታ​መነ እው​ነ​ተኛ ነው።


ዕው​ቀት እንደ ተሰ​ጠው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


ሳሙ​ኤ​ልም ሳኦ​ልን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በመ​ስ​ማት ደስ እን​ደ​ሚ​ለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ቃ​ጠ​ልና በሚ​ታ​ረድ መሥ​ዋ​ዕት ደስ ይለ​ዋ​ልን? እነሆ፥ መታ​ዘዝ ከመ​ሥ​ዋ​ዕት፥ ማዳ​መ​ጥም የአ​ውራ በግ ስብ ከማ​ቅ​ረብ ይበ​ል​ጣል።


“እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ሁሉ ታደ​ር​ገው ዘንድ ጠብቅ፤ ምንም በእ​ርሱ ላይ አት​ጨ​ምር፤ ከእ​ር​ሱም ምንም አታ​ጕ​ድል።


ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቀ​ረቡ ጊዜ ይታ​ጠቡ ነበር።


ድን​ኳ​ኑ​ንም፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ ወደ ሙሴ አመጡ፤ መያ​ዣ​ዎ​ቹን፥ ሳን​ቆ​ቹን፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹን፥ ምሰ​ሶ​ዎ​ቹን፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው፥ በአ​ክ​ሊሉ ላይ ያን​ጠ​ለ​ጥ​ሉት ዘንድ ሰማ​ያ​ዊ​ውን ፈትል አሰ​ሩ​በት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሄዱ፤ እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እንደ አዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን፥ የቃል ኪዳ​ኑ​ንም ታቦት፥ በእ​ር​ሱም ላይ ያለ​ውን የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውን፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ዕቃ ሁሉ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


በእ​ር​ሱም ውስጥ የም​ስ​ክ​ሩን ታቦት ታኖ​ራ​ለህ፤ ታቦ​ቱ​ንም በመ​ጋ​ረጃ ትጋ​ር​ዳ​ለህ።


በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛ​ውም ዓመት ቡል በሚ​ባል በስ​ም​ን​ተ​ኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍ​ሎ​ቹና እንደ ሥር​ዐቱ ሁሉ ተጨ​ረሰ። በሰ​ባት ዓመ​ትም ሠራው።


ኪራ​ምም ምን​ቸ​ቶ​ች​ንና መጫ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ድስ​ቶ​ች​ንም ሠራ፤ ኪራ​ምም ለን​ጉሡ ለሰ​ሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሠ​ራ​ውን ሥራ ሁሉ ጨረሰ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios