ዘዳግም 4:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነና ከእርሱም ሌላ አምላክ እንደ ሌለ እንድታውቅ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ መሆኑን፣ ከርሱም በቀር ሌላ አምላክ አለመኖሩን ታውቁ ዘንድ እነዚህን ነገሮች እንድታዩ ተደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም አምላካችሁ እንደሆነ እንድታውቁ ይህ ለእናንተ ተገልጧል፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ እርሱ ብቻ እንደ ሆነና ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያረጋግጥላችሁ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ አሳይቶአችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቅ ዘንድ ይህ ለአንተ ተገለጠ፤ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም። |
ስለዚህም አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እንዳንተ ያለ የለምና፥ በጆሮአችንም እንደ ሰማን ሁሉ ከአንተ በቀር አምላክ የለምና አንተ ታላቅ ነህ።
እንግዲህም አምላካችን አቤቱ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነን።”
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
በምድር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ ታውቅ ዘንድ በሰውነትህ፥ በአገልጋዮችህም፥ በሕዝብህም ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ በዚህ ጊዜ እልካለሁ።
ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ፥ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮች ሁኑ፤ እኔም ምስክር እሆናችኋለሁ ይላል እግዚአብሔር አምላክ፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልነበረም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም።
የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።
ራሳችሁን አትደብቁ፤ ከጥንት ጀምሮ አልሰማችሁምን? አልነገርኋችሁምን? ከእኔ ሌላ አምላክ እንደ ሌለ ምስክሮች ናችሁ።”
ሰማይን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።
አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም፥ ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ ዕወቅ፤