Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 6:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እስራኤል ሆይ ስማ፤ እግዚአብሔር አምላካችን፣ እግዚአብሔር አንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “እስራኤል ሆይ፥ ስማ! ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “እስራኤል ሆይ! ይህን አስታውስ! እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 6:4
26 Referencias Cruzadas  

ኤል​ያ​ስም ወደ ሕዝቡ ሁሉ ቀርቦ፥ “እስከ መቼ በሁ​ለት አሳብ ታነ​ክ​ሳ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ፤ በዓ​ልም አም​ላክ ቢሆን እር​ሱን ተከ​ተሉ” አለ። ሕዝ​ቡም አን​ዲት ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም።


እን​ዲሁ የን​ጉሡ የሕ​ዝ​ቅ​ያስ ብላ​ቴ​ኖች ወደ ኢሳ​ይ​ያስ መጡ።


ንጉሡ ዳዊ​ትም በጉ​ባ​ኤው ሁሉ ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገነ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “አቤቱ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አባ​ታ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ቡሩክ ነህ።


እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ይዘው በይ​ሁዳ ያስ​ተ​ምሩ ነበር፤ ወደ ይሁ​ዳም ከተ​ሞች ሁሉ ተመ​ላ​ል​ሰው ሕዝ​ቡን አስ​ተ​ማሩ።


ዕዝ​ራም እን​ዲህ አለ፥ “አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነህ፤ ሰማ​ዩ​ንና የሰ​ማ​ያት ሰማ​ይን፥ ሠራ​ዊ​ታ​ቸ​ው​ንም ሁሉ፥ ምድ​ር​ንና በእ​ር​ስዋ ላይ ያሉ​ትን ሁሉ፥ ባሕ​ሮ​ቹ​ንና በእ​ነ​ርሱ ውስጥ ያለ​ውን ሁሉ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ሁሉ​ንም ሕያው አድ​ር​ገ​ኸ​ዋል፤ የሰ​ማ​ዩም ሠራ​ዊት ለአ​ንተ ይሰ​ግ​ዳሉ።


አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትቈ​ጣ​ለህ? ቅን​ዐ​ት​ህም እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል?


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝ፤ ስሜ ይህ ነው፤ ክብ​ሬን ለሌላ፥ ምስ​ጋ​ና​ዬ​ንም ለተ​ቀ​ረጹ ምስ​ሎች አል​ሰ​ጥም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


ራሳ​ች​ሁን አት​ደ​ብቁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ምን? አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ምን? ከእኔ ሌላ አም​ላክ እንደ ሌለ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።”


እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፣ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’


እር​ሱም መልሶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክ​ህን በፍ​ጹም ልብህ፥ በፍ​ጹም ሰው​ነ​ትህ፥ በፍ​ጹም ኀይ​ልህ፥ በፍ​ጹም ዐሳ​ብህ ውደ​ደው፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ህ​ንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው።


እኔና አብ አንድ ነን።”


ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት።


አዎን፥ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ነው፤ የተ​ገ​ዘ​ረ​ውን በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድቅ፥ ያል​ተ​ገ​ዘ​ረ​ው​ንም በእ​ም​ነት የሚ​ያ​ጸ​ድ​ቀው እርሱ አንዱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና።


በሁሉ ሙሉ የሚ​ሆን ሁሉም ከእ​ርሱ የተ​ገኘ ከሁ​ሉም በላይ ያለ የሁሉ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አንድ ነው።


እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላይ በሰ​ማይ በታ​ችም በም​ድር አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደ ሌለ ዛሬ ዕወቅ፤ በል​ብ​ህም ያዝ።


“ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ።


አንድ እግዚአብሔር አለና፤ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፤ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤


እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ፤ ይንቀጠቀጡማል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos