Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ነገሥት 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እን​ግ​ዲ​ህም አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነን።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አሁንም እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ መሆንህን ያውቁ ዘንድ፣ ከእጁ አድነን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ በመታደግ አድነን።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ በመታደግ አድነን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እንግዲህም አምላካችን አቤቱ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር አምላክ እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ እንድታድነን እለምንሃለሁ።”

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 19:19
17 Referencias Cruzadas  

አንተ በማ​ደ​ሪ​ያህ በሰ​ማይ ስማ፤ የም​ድ​ርም አሕ​ዝብ ሁሉ ስም​ህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝ​ብህ እንደ እስ​ራ​ኤል ይፈ​ሩህ ዘንድ፥ በዚ​ህም በሠ​ራ​ሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እን​ግ​ዳው የሚ​ለ​ም​ን​ህን ሁሉ አድ​ርግ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪ​ያው ወደ ኤል​ያስ መጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፦


ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የሚ​ኖሩ ሁሉ ሰም​ተው ይከ​ብ​ቡ​ናል፤ ከም​ድ​ርም ያጠ​ፉ​ናል፤ ለታ​ላቁ ስም​ህም የም​ታ​ደ​ር​ገው ምን​ድር ነው?”


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ጸለየ፥ “በኪ​ሩ​ቤል ላይ የም​ት​ቀ​መጥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ አቤቱ፥ አንተ ብቻ​ህን የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አም​ላክ ነህ፤ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጥ​ረ​ሃል ።


ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኀይል ጠን​ካራ እንደ ሆነች የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ዲ​ያ​ውቁ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በሥ​ራው ሁሉ እን​ድ​ት​ፈሩ ነው።”


ታላ​ቁን ስም​ህን፥ ብር​ቱ​ይ​ቱ​ንም እጅ​ህን፥ የተ​ዘ​ረ​ጋ​ች​ው​ንም ክን​ድ​ህን ሰም​ተው ቢመ​ጡና በዚህ ቤት ቢጸ​ልዩ፥


የም​ድር አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ከእ​ር​ሱም በቀር ሌላ እንደ ሌለ ያውቁ ዘንድ፥


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት የዘ​መ​ር​ዋት መዝ​ሙር ይህች ናት፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ስሙ​ንም ጥሩ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ሥራ​ውን አውሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታው​ቃ​ለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወ​ን​ዙን ውኃ በእጄ ባለ​ችው በትር እመ​ታ​ለሁ፤ ውኃ​ውም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።


እር​ሱም ከጭ​ፍ​ራው ሁሉ ጋር ወደ ኤል​ሳዕ ተመ​ለሰ፤ ወደ እር​ሱም ደርሶ በፊቱ ቆመና፥ “እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነው እንጂ በም​ድር ሁሉ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ዐወ​ቅሁ፤ አሁ​ንም ከአ​ገ​ል​ጋ​ይህ በረ​ከት ተቀ​በል” አለው።


ከእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሮ​ችና ከዚህ እው​ነት በኋላ የአ​ሦር ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ በተ​መ​ሸ​ጉ​ትም ከተ​ሞች ፊት ሰፈረ፤ ሊወ​ስ​ዳ​ቸ​ውም አሰበ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios