ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
ዘዳግም 30:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፊትህ ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና መርገምን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ እኔ በሕይወትና በሞት መካከል፥ በእግዚአብሔር በረከትና መርገም መካከል ምርጫ እሰጣችኋለሁ፤ በምታደርጉትም ምርጫ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ ምስክር አድርጌ እጠራለሁ፤ ስለዚህም እናንተና ዘሮቻችሁ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤ |
ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያሳየውና ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
እግዚአብሔር ለጃንደረቦች እንዲህ ይላል፥ “ሰንበቴን ቢጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ቢመርጡ፥ በቃል ኪዳኔም ጸንተው ቢኖሩ፥
ለዚህም ሕዝብ እንዲህ በል፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በፊታችሁ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ አድርጌአለሁ።
ለእነርሱም፥ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘለዓለም እንዲፈሩኝ ሌላ መንገድና ሌላ ልብ እሰጣቸዋለሁ።
እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፤ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
“እንዲህም ይሆናል፤ እኔ በፊትህ ያኖርሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረከቱና መርገሙ በወረደብህ ጊዜ፥ አምላክህ እግዚአብሔር በሚበትንህ በዚያ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ሆነህ በልብህ ዐስበው፤
ዛሬ እኔ የማዝዝህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ብትሰማ፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም ብትወድድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ብትሄድ፥ ሥርዐቱንና ፍርዱንም ብትጠብቅ በሕይወት ትኖራለህ፤ በቍጥርም ትበዛለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ልትወርሳት በምትሄድባት በምድሪቱ ሁሉ ይባርክሃል።
በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል፤ እተዋቸውማለሁ፤ ፊቴንም ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም መብል ይሆናሉ፤ በዚያም ቀን፦ በእውነት አምላካችን እግዚአብሔር ትቶናልና፥ በእኛም መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል።
ይህን ቃል በጆሮአቸው እነግር ዘንድ፥ ሰማይንና ምድርንም አስመሰክርባቸው ዘንድ የነገዶቻችሁን አለቆች፥ ሽማግሌዎቻችሁን ሁሉ፥ ሹሞቻችሁንም፥ ጻፎቻችሁንም ሰብስቡልኝ፤
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
“ልጆችን፥ የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ረዥም ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በበደላችሁም ጊዜ፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል ባደረጋችሁ ጊዜ፥ ታስቈጡትም ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ፥
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አትቀመጡባትም።
ጠብቁት፤ አድርጉትም፤ ይህን ሥርዐት ሁሉ ሰምተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤
እናንተ፥ ልጆቻችሁም፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዕድሜአችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፈርታችሁ እኔ ለእናንተ ያዘዝሁትን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ፥ ዕድሜአችሁም ይረዝም ዘንድ፤
አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ ማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።