Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 42:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እኔም ዛሬ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እና​ን​ተም በላ​ከኝ ነገር ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እነሆ፤ ዛሬ በግልጽ ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ልኮኝ የነገርኋችሁን ሁሉ አሁንም አልታዘዛችሁም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እኔም ዛሬ ነገርኋችሁ፥ እናንተ ግን ወደ እናንተ በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የጌታን ድምፅ አልሰማችሁም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እነሆ ዛሬ እኔም መልሱን ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድነግራችሁ በእኔ አማካይነት ለላከላችሁ ቃል ሁሉ ታዛዦች አልሆናችሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፥ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 42:21
16 Referencias Cruzadas  

እነ​ርሱ ዐመ​ፀኛ ቤት ስለ​ሆኑ ቢሰሙ ወይም ቢደ​ነ​ግጡ ቃሌን ትነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ የአ​ፌን ቃል ስማ፤ በቃ​ሌም ገሥ​ጻ​ቸው።


“የዚ​ህ​ንም ርግ​ማን ቃሎች በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ በልቡ ‘ይህን በልቤ ስን​ፍና በማ​ድ​ረግ ሄጃ​ለ​ሁና ይቅር ይለ​ኛል’ የሚል ቢኖር የበ​ደ​ለኛ ፍዳ ካል​በ​ደለ ጋር እን​ዳ​ይ​ተ​ካ​ከል፥


የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ፥ ለእ​ነ​ርሱ አም​ላ​ካ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከ​ውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤር​ም​ያስ ለሕ​ዝቡ ሁሉ መና​ገ​ርን በፈ​ጸመ ጊዜ እን​ዲህ ሆነ፤


የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ይቀ​መጡ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።


“እነሆ፥ ዛሬ በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ መል​ካ​ም​ነ​ት​ንና ክፉ​ነ​ትን አኑ​ሬ​አ​ለሁ።


በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥሁ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በአ​ንተ ላይ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ አን​ተና ዘርህ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ ሕይ​ወ​ትን ምረጥ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል አል​ሰ​ሙ​ምና ወደ ግብፅ ምድር ገቡ፤ እስከ ጣፍ​ናስ ድረ​ስም መጡ።


ሕዝብ እን​ደ​ሚ​መጣ ወደ አንተ ይመ​ጣሉ፤ እንደ ሕዝ​ቤም በፊ​ትህ ይቀ​መ​ጣሉ፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ፤ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸው ሐሰት ነገር አለና፥ ልባ​ቸ​ውም ጣዖ​ታ​ትን ይከ​ተ​ላ​ልና።


እነሆ አንተ መል​ካም ድምፅ እን​ዳ​ለው እን​ደ​ሚ​ወ​ደድ መዝ​ሙር ማለ​ፊ​ያም አድ​ርጎ በገና እን​ደ​ሚ​ጫ​ወት ሰው ሁነ​ህ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቃል​ህ​ንም ይሰ​ማሉ ነገር ግን አያ​ደ​ር​ጉ​ትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios