Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ጢሞቴዎስ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ ማዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በእግዚአብሔርና በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት እነዚህን ትእዛዞች ያለ አድልዎ እንድትጠብቅና አንዳችም ነገር በማበላለጥ እንዳታደርግ ዐደራ እልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አንዱን ከሌላው በማበላለጥ ምንም ዓይነት ነገር ሳታደርግ፥ ያለ አድልዎ እነዚህን ትዛዛቶች እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በተመረጡትም መላእክት ፊት አደራ እልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በምታደርገው ነገር ሁሉ አንዱን ከሌላው ሳታበላልጥ ወይም ለማንም ሳታዳላ ይህን ምክሬን ሁሉ እንድትፈጽም በእግዚአብሔርና በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት ዐደራ እልሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አንድን እንኳ በአድልዎ ሳታደርግ፥ እነዚህን ያለ መዘንበል እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት እመክርሃለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ጢሞቴዎስ 5:21
25 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ኀጢአትን ላደረጉ መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ጥሎ በጨለማ ጉድጓድ ለፍርድ ሊጠበቁ አሳልፎ ከሰጣቸው፥


በእግዚአብሔር ፊት፥ በሕያዋንና በሙታንም ሊፈርድ ባለው በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት፥ በመገለጡና በመንግሥቱም እመክርሃለሁ፤


ሁሉን በሕይወት በሚጠብቅ በእግዚአብሔር ፊት፥ በጴንጤናዊውም በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።


ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።


ስለ​ዚህ ከአ​ሁን ጀምሮ በሥጋ የም​ና​ው​ቀው የለም፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በሥጋ ብና​ው​ቀው አሁን ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የም​ና​ው​ቀው አይ​ደ​ለም።


በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል ‘እናንተ ርጉማን! ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።


እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፤ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል።


ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


ይህ መልእክት ለቅዱሳን ወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አምላችኋለሁ።


እነ​ር​ሱም እን​ዲህ ብለው ጠየ​ቁት፥ “መም​ህር ሆይ፥ አንተ እው​ነት እን​ደ​ም​ት​ና​ገ​ርና እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ፊት አይ​ተ​ህም እን​ደ​ማ​ታ​ዳላ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ገድ በቀ​ጥታ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር እና​ው​ቃ​ለን።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።


ስለዚህ መንገዴን እንዳልጠበቃችሁ፥ በሕግም ለሰው ፊት እንዳዳላችሁ መጠን፥ እኔ ደግሞ በሕዝብ ሁሉ ፊት የተናቃችሁና የተዋረዳችሁ አድርጌአችኋለሁ።


የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥


እና​ቱ​ንና አባ​ቱን አላ​የ​ኋ​ች​ሁም ላለ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ላላ​ወቀ፥ ልጆ​ቹ​ንም ላላ​ስ​ተ​ዋለ፤ ቃል​ህን ለጠ​በቀ፥ በቃል ኪዳ​ን​ህም ለተ​ማ​ጠነ።


ተመ​ል​ሳ​ችሁ ተጓዙ፤ ወደ አሞ​ራ​ው​ያን ተራራ፥ ወደ አረ​ባም ሀገ​ሮች ሁሉ፥ በተ​ራ​ራ​ውም፥ በሜ​ዳ​ውም፥ በሊ​ባም፥ በባ​ሕ​ርም ዳር ወዳሉ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ ወደ ሊባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ ሂዱ።


“በፍ​ርድ ዐመፃ አታ​ድ​ርጉ፤ ለድሃ አታ​ድላ፤ ባለ​ጠ​ጋ​ው​ንም አታ​ክ​ብር፤ ነገር ግን ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ በእ​ው​ነት ፍረድ።


በእ​ኔና በቃሌ የሚ​ያ​ፍር ሁሉ የሰው ልጅ በክ​ብሩ፥ በአ​ባ​ቱም ክብር፥ ቅዱ​ሳ​ን​መ​ላ​እ​ክ​ትን አስ​ከ​ትሎ ሲመጣ ያፍ​ር​በ​ታል።


በእ​ነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች ስፍራ ሌሎች ድን​ጋ​ዮ​ችን ያገ​ባሉ፤ ሌላም ጭቃ ወስ​ደው ቤቱን ይመ​ር​ጉ​ታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios