Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 12:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 በጽድቅ መንገድ ሕይወት አለ፥ ክፉን የሚያስቡ ሰዎች መንገዶች ግን ወደ ሞት ያወርዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ፤ በዚያ ጐዳና ላይ ሞት የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ በጎዳናዋም ሞት የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እውነተኛነት የሕይወት መንገድ ነው፤ ክፋት ግን የሞት መንገድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 12:28
17 Referencias Cruzadas  

የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው።


የሀብት ድልብ ለኃጥኣን አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች።


ጻድቅ ልጅ ለሕይወት ይወለዳል፤ የኃጥኣን መወለድ ግን ለሞት ነው።


መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። እኔን ያገኘ ሕይወትን አገኘ፤ ፈቃዱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይዘጋጃል።


በዚህ ሥርዐት ብዙ ዘመን ትኖራለህ፥ የሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል።


ለዚ​ህም ሕዝብ እን​ዲህ በል፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በፊ​ታ​ችሁ የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ገ​ድና የሞ​ትን መን​ገድ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ።


በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እው​ነ​ት​ንም ለማ​ድ​ረግ ፍር​ዴን ቢጠ​ብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ኀጢ​አ​ትም ሞትን እንደ አነ​ገ​ሠ​ችው እን​ዲሁ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ጽድ​ቅን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ታነ​ግ​ሠ​ዋ​ለች።


“እነሆ፥ ዛሬ በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ መል​ካ​ም​ነ​ት​ንና ክፉ​ነ​ትን አኑ​ሬ​አ​ለሁ።


በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥሁ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በአ​ንተ ላይ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ አን​ተና ዘርህ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ ሕይ​ወ​ትን ምረጥ፤


እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የዚ​ህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ይጠ​ብ​ቁና ያደ​ርጉ ዘንድ ልጆ​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ታ​ዝ​ዙ​በት ዛሬ የም​መ​ሰ​ክ​ር​ላ​ች​ሁን ቃል ሁሉ በል​ባ​ችሁ አኑ​ሩት።


ጻድቅ እንደ ሆነ ካወቃችሁ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከእርሱ እንደ ተወለደ እወቁ።


ልጆች ሆይ፥ ማንም አያስታችሁ፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።


ወዳጅ ሆይ! በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos