ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም ጻፎችና ፈራጆች ነበሩ።
ዘዳግም 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በሀገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና መባውን የሚጽፉትን ሹሙ፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድን ይፍረዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በጽድቅ ፍርድ ይዳኙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ከተሞች ሁሉ ለየነገዶችህ ዳኞችንና አለቆችን ሹም፤ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክህ እግዚአብሔር ለየነገድህ በሚሰጠው ምድር በእያንዳንዱ ከተማ ዳኞችና ሌሎችንም ባለሥልጣኖች ትሾማለህ፤ እነዚህም ሰዎች ለሕዝቡ ያለ አድልዎ መፍረድ ይገባቸዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በአገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና አለቆችን ሹም፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድ ይፍረዱ። |
ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም ጻፎችና ፈራጆች ነበሩ።
አንተም ዕዝራ፥ በእጅህ እንዳለው እንደ አምላክህ ጥበብ መጠን በወንዝ ማዶ ባሉ ሕዝብ ሁሉ፥ የአምላክህን ሕግ በሚያውቁ ሁሉ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ጻፎችንና ፈራጆችን ሹም፤ የማያውቁትንም አስተምሩአቸው።
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ ኀያላን ሰዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን እውነተኞች ሰዎችን፥ ትዕቢትንም የሚጠሉ ሰዎችን ፈልግ። ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የዐሥርም አለቆችን ሹምላቸው።
“ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ ያረገዘችንም ሴት ቢያቈስሉ ተሥዕሎተ መልክእ ያልተፈጸመለት ፅንስም ቢያስወርዳት፥ የሴቲቱ ባል የጣለበትን ያህል ካሳ ይክፈል፤
ጌታው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ፈራጆች ይውሰደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃኑም አቅርቦ አፍንጫውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ባሪያው ይሁነው።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጅህን አትታይ። አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ በረከት መጠን እያንዳንዳችሁ እንደ ችሎታችሁ ታመጣላችሁ።
ፍርድን አታጣምም፤ ፊት አይተህም አታድላ፤ ጉቦን አትቀበል፥ ጉቦ የጥበበኞችን ዐይን ያሳውራልና፥ የእውነትንም ቃል ያጣምማልና ጉቦ አትቀበል።
ማናቸውም ሰው ቢኰራ፥ በአምላክህ እግዚአብሔር ስም ለማገልገል የሚቆመውን ካህኑን ወይም በዚያ ወራት ያለውን ፈራጁን ባይሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእስራኤልም ዘንድ ክፉውን አስወግዱ፤