ቈላስይስ 2:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመታለልና ራስን ዝቅ በማድረግ ለመላእክት አምልኮ ትታዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአላየውም በከንቱ የሥጋው ምክር እየተመካ የሚያሰንፋችሁ አይኑር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐጕል ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ የሚወድድ ማንም ሰው እንዳያደናቅፋችሁ ተጠንቀቁ። እንደዚህ ያለ ሰው ስላየው ራእይ ከመጠን በላይ ራሱን እየካበ በሥጋዊ አእምሮው ከንቱ ሐሳብ ተሞልቶ ይታበያል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራስን ማዋረድና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባየውም ራእይ ላይ በጽኑ እየተመረኮዘ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአጉል ትሕትናና መላእክትን በማምለክ የሚመካ ማንም ሰው ያለ ዋጋ እንዳያስቀራችሁ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ዐይነቱ ሰው ስለሚያየው ራእይ እየተመጻደቀ ከንቱና ሥጋዊ በሆነ አስተሳሰብ ይታበያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትሕትናንና የመላእክትን አምልኮ እየወደደ፥ ባላየውም ያለ ፈቃድ እየገባ፥ በሥጋዊም አእምሮ በከንቱ እየታበየ ማንም አይፍረድባችሁ፤ |
ዝሙትሽን ከእነርሱ ጋር አበዛሽ፤ ከአንቺ የራቁ ብዙዎችንም ተጐዳኘሽ። መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፤ ከእነርሱም ጋር ተወገድሽ፤ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።
ስለ ምድያም አለቃ ልጅ ስለ እኅታቸው ስለ ከስቢ በፌጎር ምክንያት በሸነገሉአችሁ ሽንገላ አስጨንቀዋችኋልና።”
የእግዚአብሔርን እውነት ሐሰት አድርገዋታልና፤ ተዋርደውም ፍጥረቱን አምልከዋልና፤ ሁሉን የፈጠረውን ግን ተዉት፤ እርሱም ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤ አሜን።
እነርሱ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ያይደለ ለሆዳቸው ይገዛሉና፤ በነገር ማታለልና በማለዛዘብም የብዙዎች የዋሃንን ልብ ያስታሉ፤
በሥጋዊ ሕግም ትኖራላችሁና እርስ በርሳችሁ የምትቃኑና የምትከራከሩ ከሆነ ግን ሥጋውያን መሆናችሁ አይደለምን? እንደ ሰው ልማድስ የምትኖሩ መሆናችሁ አይደለምን?
ወንድሞቻችን ሆይ! እኔም፥ አጵሎስም ብንሆን መከራ የተቀበልነው ስለ እናንተ ነው፤ እናንተ እንድትማሩ፥ ከመጻሕፍት ቃልም ወጥታችሁ በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳትታበዩ ነው።
ለጣዖታት ስለሚሠዉ መሥዋዕቶች ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን እናውቃለን፤ ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።
በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሽቀዳደሙ ሁሉ እንደሚፋጠኑ አታውቁምን? ለቀደመው የሚደረግለት ዋጋ አለ፤ እንዲሁ እናንተም እንድታገኙ ፈጽማችሁ ሩጡ።
ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰሉ እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ከክርስቶስ የዋህነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ።
ነገር ግን ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ እንደምወደው ሆናችሁ ያላገኘኋችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እንደማትወዱት እሆንባችኋለሁ ብዬ እፈራለሁ፤ ወይም እኮ በመካከላችሁ ክርክር፥ ኵራት፥ መቀናናት፥ መበሳጨት፥ መዘባበት፥ ወይም መተማማት፥ መታወክ፥ ወይም ልብን ማስታበይ ይኖር ይሆናል።
እንግዲህ በልባቸው ከንቱ አሳብ እንደሚኖሩ እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ይህን እላለሁ፤ በእግዚአብሔርም እመሰክራለሁ።
በከንቱ ነገርም የሚያስታችሁ አይኑር፤ በእርሱ ምክንያት በከሓዲዎች ልጆች ላይ የእግዚአብሔር መዓት ይመጣልና።
“ምስጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛና ለልጆቻችን ለዘለዓለም ነው።
የኋላዬን እረሳለሁና፥ ወደ ፊቴም ፈጥኜ እገሠግሣለሁና፤ በኢየሱስ ክርስቶስም ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን የጥሪ ዋጋ ለማግኘት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።
ይህም ስለ ልብ ትሕትናና እግዚአብሔርንም ስለ መፍራት፥ ለሥጋ ስለ አለማዘን ጥበብን ይመስላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለውም።
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።
መንፈስ ግን በግልጥ “በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ፤” ይላል፤ በገዛ ሕሊናቸው እንደሚቃጠሉ ደንዝዘው፥
ምንዝር የሞላባቸው ኀጢአትንም የማይተዉ ዐይኖች አሉአቸው፤ የማይጸኑትን ነፍሳት ያታልላሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ናቸው።
ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።
ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።