ቈላስይስ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ይህም ስለ ልብ ትሕትናና እግዚአብሔርንም ስለ መፍራት፥ ለሥጋ ስለ አለማዘን ጥበብን ይመስላል፤ ነገር ግን ከሥጋ በላይ ነው እንጂ ምንም ክብር የለውም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 እነዚህ ነገሮች በገዛ ራስ ላይ ከሚፈጥሩት የአምልኮ ስሜት፣ ከዐጕል ትሕትናና ሰውነትን ከመጨቈን አንጻር በርግጥ ጥበብ ያለባቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን የሥጋን ልቅነት ለመቈጣጠር አንዳች ፋይዳ የላቸውም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 እነዚህም በገዛ ፈቃድ የሚደረግ አምልኮንና ራስን ማዋረድ ሥጋንም የመጨቆን ጥበብ ያላቸው ይመስላሉ፤ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅሙም። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 እነዚህ ትእዛዞች ከገዛ ፈቃድ በመነጨ አምልኮና በአጉል ትሕትና፥ ሰውነትንም በማጐሳቈል ላይ ስለሚያተኲሩ ጥበብ ያላቸው ይመስሉ ይሆናል፤ ነገር ግን ሥጋዊ ስሜትን በመቈጣጠር ረገድ ዋጋቢሶች ናቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 ይህ እንደ ገዛ ፈቃድህ በማምለክና በትሕትና ሥጋንም በመጨቆን ጥበብ ያለው ይመስላል፥ ነገር ግን ሥጋ ያለ ልክ እንዳይጠግብ ለመከልከል ምንም አይጠቅምም። Ver Capítulo |