ቤቱም በተሠራ ጊዜ ፈጽመው በተወቀሩ ድንጋዮች ተሠራ፤ ሲሠሩትም መራጃና መጥረቢያ፥ የብረትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አልተሰማም።
ቈላስይስ 1:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በብርሃን ቅዱሳን ለሚታደሉት ርስት የበቃን ያደረገንን እግዚአብሔር አብን አመስግኑት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቅዱሳን ርስት በብርሃን ተካፋዮች ለመሆን ያበቃንን አብን እንድታመሰግኑ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብርሃን የቅዱሳንን ርስት እንድንካፈል ያበቃንን አብን እንድታመሰግኑት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም በብርሃን መንግሥት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ርስት እንድትካፈሉ ያበቃችሁን እግዚአብሔር አብን በደስታ አመስግኑት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ፥ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ፥ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን። |
ቤቱም በተሠራ ጊዜ ፈጽመው በተወቀሩ ድንጋዮች ተሠራ፤ ሲሠሩትም መራጃና መጥረቢያ፥ የብረትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አልተሰማም።
ዳዊትም ጉባኤውን ሁሉ፥ “አምላካችን እግዚአብሔርን አመስግኑ” አላቸው። ጉባኤውም ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፥ በጕልበታቸውም ተንበርክከው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ደግሞም ለንጉሡ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ፥ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።
ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ በመንፈስና በእውነት ለአብ የሚሰግዱባት ጊዜ ትመጣለች፤ እርስዋም አሁን ናት። አብ እንዲህ የሚሰግዱለትን ይሻልና።
አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፥ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
ከቅርንጫፎችዋ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ የዱር ወይራ የሆንህ አንተን በእነርሱ ፋንታ ተከሉ፤ የእነርሱንም ሥርነት አገኘህ፤ እንደ እነርሱም ዘይት ሆንኽ።
የሚገባቸውም ሰለሆነ በመንፈሳዊ ሥራ አሕዛብን ከተባበሩአቸው ለሰውነታቸው በሚያስፈልጋቸው ሊረዱአቸው ይገባል።
እና የእግዚአብሔር ልጆች ከሆን ወራሾቹ ነን፤ የእግዚአብሔር ወራሾች ከሆንም የክርስቶስ ወራሾቹ ነን፤ በመከራ ከመሰልነውም በክብር እንመስለዋለን።
ዳግመናም የክብሩን ባለጠግነት ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ ለወደዳቸውና ለጠራቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የምሕረት መላእክትን ያመጣል።
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።
ዐይነ ልቡናችሁንም ያበራላችሁ ዘንድ፥ የተጠራችሁበት ተስፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅዱሳንም የርስቱ ክብር ባለጸግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥
አሕዛብን ወራሾቹና አካሉ ያደርጋቸው ዘንድ፥ በወንጌልም ትምህርት በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ተስፋ አንድ ይሆኑ ዘንድ።
የሚያሳፍር ነገርም፥ የስንፍና ነገርም፥ ወይም የማይገባ የዋዛ ነገር በእናንተ ዘንድ አይሁን፤ ማመስገን ይሁን እንጂ።
ይኸውም ልቡናቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትምህርታቸውም በማወቅ፥ በፍቅርና ፍጹምነት ባለው ባለጸግነት፥ በጥበብና በሃይማኖት፥ ስለ ክርስቶስም የሆነውን የእግዚአብሔርን ምክር በማወቅ ይጸና ዘንድ ነው።
በቃልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ፤ ስለ እርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑት።
መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥
አሁንም ከሰማያዊ ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞቻችን ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ።
እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።
ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።