Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 9:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ዳግ​መ​ናም የክ​ብ​ሩን ባለ​ጠ​ግ​ነት ሊያ​ሳይ ቢወድ አስ​ቀ​ድሞ ለወ​ደ​ዳ​ቸ​ውና ለጠ​ራ​ቸው ለይ​ቅ​ርታ የተ​ዘ​ጋጁ የም​ሕ​ረት መላ​እ​ክ​ትን ያመ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው፣ የምሕረቱም መግለጫዎች ለሆኑት፣ የክብሩ ባለጠግነት እንዲታወቅ ይህን አድርጎ እንደሆነስ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ይህም አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው በምሕረት ዕቃዎች ላይ የክብሩን ባለጠግነት እንዲገልጥ ቢሆንስ?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ይህንንም ያደረገው አስቀድሞ ለክብር ላዘጋጃቸው ለምሕረት ዕቃዎች የክብሩን ብዛት ለመግለጥ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 9:23
22 Referencias Cruzadas  

ወይስ በቸ​ር​ነቱ ብዛት በመ​ታ​ገሡ፥ ለአ​ን​ተም እሺ በማ​ለቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ዋቂ ልታ​ደ​ር​ገው ታስ​ባ​ለ​ህን? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርስ ቸር​ነቱ አን​ተን ወደ ንስሓ እን​ዲ​መ​ል​ስህ አታ​ው​ቅ​ምን?


እንደ ጌት​ነቱ ምላት ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም ኀይል ያጸ​ና​ችሁ ዘንድ።


እን​መ​ላ​ለ​ስ​በት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ ላዘ​ጋ​ጀው በጎ ሥራ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ የፈ​ጠ​ረን ፍጥ​ረቱ ነንና።


እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል።


ዛሬ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዚ​ህን ምክር የክ​ብር ባለ​ጸ​ግ​ነት በአ​ሕ​ዛብ ላይ እን​ዲ​ገ​ል​ጽ​ላ​ቸው ለፈ​ቀ​ደ​ላ​ቸው ለቅ​ዱ​ሳን ተገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፤ የም​ን​ከ​ብ​ር​በት አለ​ኝ​ታ​ችን በእ​ና​ንተ አድሮ ያለ ክር​ስ​ቶስ ነውና።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ይቅር ስላ​ለን የጸ​ጋ​ውን ባለ​ጠ​ግ​ነት ብዛት በሚ​መ​ጣው ዓለም ይገ​ልጥ ዘንድ፥


ዐይነ ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ያበ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ተስ​ፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም የር​ስቱ ክብር ባለ​ጸ​ግ​ነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥


ልጁ በብ​ዙ​ዎች ወን​ድ​ሞች መካ​ከል በኵር ይሆን ዘንድ አስ​ቀ​ድሞ ያወ​ቃ​ቸ​ው​ንና የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ልጁን ይመ​ስሉ ዘንድ አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።


እር​ሱም የአ​ባ​ቶ​ችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከ​ሓ​ድ​ያ​ን​ንም ዐሳብ ወደ ጻድ​ቃን ዕው​ቀት ይመ​ልስ ዘንድ፥ ሕዝ​ብ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ዘ​ጋጀ ያደ​ርግ ዘንድ በኤ​ል​ያስ መን​ፈ​ስና ኀይል በፊቱ ይሄ​ዳል።”


አቤቱ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ሆይ፥ ይህን አሳብ በሕ​ዝ​ብህ ልብ ላይ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብቅ፤ ልባ​ቸ​ው​ንም ወደ አንተ አቅና።


እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፤ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ።


በብ​ር​ሃን ቅዱ​ሳን ለሚ​ታ​ደ​ሉት ርስት የበ​ቃን ያደ​ረ​ገ​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።


ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና።


ያዘ​ጋ​ጃ​ቸ​ውን እነ​ር​ሱን ጠራ፤ የጠ​ራ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን አጸ​ደቀ፤ የአ​ጸ​ደ​ቃ​ቸ​ው​ንም እነ​ር​ሱን አከ​በረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios