እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘቅተ መሐላም መጣ፤ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ።
ሐዋርያት ሥራ 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እርሱም አባቶቻችንም ሞቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም አባቶቻችንም በዚያ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም ሞተ፤ አባቶቻችንም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብጽ ሄደ፤ እርሱና አባቶቻችን እዚያ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ወደ ግብፅ ወረደ እርሱም ሞተ አባቶቻችንም፤ |
እስራኤልም ለእርሱ ያለውን ሁሉ ይዞ ተነሣ፤ ወደ ዐዘቅተ መሐላም መጣ፤ መሥዋዕትንም ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ ሠዋ።
ከአባቶችም ጋር በአንቀላፋሁ ጊዜ ከግብፅ ምድር አውጥተህ ትወስደኛለህ፤ በአባቶችም መቃብር ትቀብረኛለህ።” እርሱም፥ “እንደ ቃልህ አደርጋለሁ” አለ። እርሱም፥ “ማልልኝ” አለው።
እንዳያጠፋቸው የቍጣውን መቅሠፍት ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ባጠፋቸው ነበር አለ።
ሙሴም የዮሴፍን ዐጽም ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ “እግዚአብሔር መጐብኘትን በጐበኛችሁ ጊዜ ዐጽሜን ውሰዱ፤ ከእናንተም ጋር ከዚህ አውጡ” ብሎ የእስራኤልን ልጆች አምሎአቸው ነበርና።
አባቶችህ ሰባ ነፍስ ሆነው ወደ ግብፅ ወረዱ፤ አሁን ግን አምላክህ እግዚአብሔር ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ።
በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ተናገር፦ አባቴ ከሶርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም በቍጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚያም ታላቅና የበረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ያወጡትን የዮሴፍን አፅም ያዕቆብ በሰቂማ ከሚኖሩ ከአሞራውያን በመቶ በጎች በገዛው ለዮሴፍ ድርሻ አድርጎ በሰጠው እርሻ በአንዱ ክፍል በሰቂማ ቀበሩት።
ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ የያዕቆብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረቱም፤ ግብፃውያንም መከራ አጸኑባቸው።